1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታንያ በሩስያ ጉዳይ አጋሮቿ አብረው እንዲቆሙ ጠየቀች

ዓርብ፣ መጋቢት 7 2010

ነዋሪነታቸው ብሪታንያ ውስጥ የኾኑት የቀድሞ የሩሲያ እና የብሪታንያ ድርብ ሠላይ ከሴት ልጃቸዉ ጋር በሩሲያ ሠራሽ የነርቭ ጋዝ ብሪታንያ ውስጥ መጠቃታቸው በሩስያ እና ብሪታንያ መካከል ያስከተለው ውዝግብ ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/2uSw9
Großbritannien Theresa May, Premierministerin
ምስል Reuters/Parliament TV

የብሪታንያና የሩስያ ውዝግብ

ነዋሪነታቸው ብሪታንያ ውስጥ የኾኑት  የቀድሞ የሩሲያ እና የብሪታንያ ድርብ ሠላይ ከሴት ልጃቸዉ ጋር በሩሲያ ሠራሽ የነርቭ ጋዝ ብሪታንያ ውስጥ መጠቃታቸው በሩስያ እና ብሪታንያ መካከል ያስከተለው ውዝግብ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት ጥቃቱ የደረሰባቸው የቀድሞው ሠላይ ሠርጌይ ስክሪፓል እና ከሞስኮ ልትጠይቃቸው የመጣችው ልጃቸው ዩሊያ ሕይወታቸው በአስጊ ኹኔታ ላይ ይገኛል። ውዝግቡ ተካሮ ብሪታንያ 23 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ለማባረር ስትወስን  በድርጊቱ እንደሌለችበት በመግለጥ አጥብቃ የምትቃወመዉ ሩሲያም በተመሳሳይ የአፀፋ ርምጃ እንደምትወስድ አሳዉቃለች። ብሪታንያ የአውሮጳ ኅብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ አጋሮቿ ከጎኗ እንዲቆሙ ትናንት ጠቅላይ ሚንሥትር ቴሬዛ ሜይ ለምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠይቃለች። ገበያው ንጉሤ ዝርዝር ዘገባውን ከብራስልስ ልኮልናል።  

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ሸዋዬ ለገሠ