1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቦልተን፤ አዲሱ የትራምፕ የፀጥታ አማካሪ

ዓርብ፣ መጋቢት 14 2010

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናል ትራምፕ ባለስልጣኖቻቸዉን መለዋወጣቸዉ መቀጠላቸዉ እየተነገረ ነው። በዛሬዉ ዕለትም የፀጥታ ጉዳይ አማካሪ የነበሩትን ኤች አር ማክማስተርን በጆን ቦልተን እንደተኳቸዉ ተዘግቧል። እንደተለመደዉ የትራምፕ ሹም ሽር ይፋ የሆነዉ በትዊተር ነው።

https://p.dw.com/p/2us4j
USA neuer Sicherheitsberater John Bolton
ምስል picture-alliance/Zumapress/M. Brochstein

አምባሳደር ጆን ቦልተን

ትራምብ በዙሪያቸዉ የሚገኙ ባለስልጣኖችን የሚለዋዉጡበት ርምጃቸዉ ሳልጣን ላይ ከወጡ ለ14ኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ተንታኞች የትራምፕ ሹም ሽር በአስተሳሰባቸዉ የሚስማሙ እና የዉጭ ፖሊሲያቸዉን እሳቸዉ የሚፈልጉትን ኃይል የቀላቀለ አካሄድ የሚፈግፉ ሰዎችን የማሰባሰቢያ ስልት እንደሆነ ይናገራሉ። ከ10 ዓመታት በፊት በተመድ የአሜሪካን አምባሳደር ሆነዉ ያገለገሉት ዲፕሎማት እና የሕግ ባለሙያ የፊታችን ሚያዝያ 1 ቀን 2010ዓ,ም አዲሱን ሥራቸዉን በይፋ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። አምባሳደር ጆን ቦልተን ማን ናቸዉ? ወደዋሽንግተን በመደወል ዘጋቢያች ከናትናኤል ወልዴ ጋር በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ