1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተመላሽ ስደተኞች፣ ኢትዮጵያ እና የአውሮጳ ህብረት

ማክሰኞ፣ ጥር 22 2010

የኢትዮጵያ መንግሥት በአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች ለመኖር ህጋዊ ፈቃድ የተከለከሉትን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መቀበል በሚችልበት ሁኔታዎች ላይ ከህብረቱ ጋር እየተደራደረ ነው።

https://p.dw.com/p/2rl4j
Symbolbild EU
ምስል Getty Images/C. Furlong

የኢትዮጵያ እና የአውሮጳ ህብረት የስደተኞች ጉዳይ ድርድር

የአውሮጳ ህብረት  የተገን ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኘ ስደተኞችን ወደ የሀገራቸው መልሶ ለመላክ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት ጋርም ስምምነት ላይ ደርሷል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች ለመኖር ህጋዊ ፈቃድ የተከለከሉትን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መቀበል በሚችልበት ሁኔታዎች ላይ ከህብረቱ ጋር  እየተደራደረ ነው። የስምምነቱ ረቂቅ ሰነድ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ይፋ ሆኖ ውይይት እና ክርክር እየተደረገበት ነው። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ሁለቱ ወገኖች ስለሚደራደሩበት የተመላሽ ስደተኞች ጉዳይ ስምምነት ይዘት እና አፈጻጸም ላይ ያተኩራል። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ አዘጋጅቶታል።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ