1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚአፍሪቃ

አብዛኛዉ የኢትዮጵያዊ ደሐ ነዉ-ጥናት

ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2016

አፍሮ ባሮ ሜትር የተባለዉ ተቋም ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እየተባባሰና የድህነት ደረጃም እየጨመረ ነዉ።በአፍሪካ ተሞክሮዎች እና ግምገማዎች በ39 ሀገሮች ላይ ገለልተኛ ሆኖ ይሰራል የሚባለው ይህ ተቋም በኢኮኖሚ፣ በግል ኑሮ ሁኔታ እና በድህነት ልኬት ላይ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተዉ ኢትዮጵያ መልካም ሁኔታ ውስጥ አይደለችም

https://p.dw.com/p/4eBHk
ኢትዮጵያ ዉስጥ በገጠር አካባቢዎች ከሚኖሩ ድኻ ቤተሰቦች አንዱ
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ኑሯቸዉ ከድሕነት ጠገግ በታች ነዉምስል Mikyas Desalle

አብዛኛዉ የኢትዮጵያዊ ደሐ ነዉ-ጥናት

 

ከ60 ከመቶ የሚበልጠዉ ኢትዮጵያዊ ደሐ መሆኑን አንድ ተቋም በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ ጥናት ጠቆመ።አፍሮ ባሮ ሜትር የተባለዉ ተቋም ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚው እየተባባሰ እና የድህነት ደረጃም እየጨመረ ነዉ።በአፍሪካ ተሞክሮዎች እና ግምገማዎች  በ39 ሀገሮች ላይ ገለልተኛ ሆኖ ይሰራል የሚባለው ይህ ተቋም በኢኮኖሚ፣ በግል ኑሮ ሁኔታ እና በድህነት ልኬት ላይ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተዉ ኢትዮጵያ መልካም ሁኔታ ውስጥ አይደለችም።
"ስልሳ አንድ በመቶው ኢትዮጵያዊ በድህነት ውስጥ ነው"


አፍሮ ባሮ ሜትር ኢትዮጵያን በተመለከተው በዚህ ሁለተኛው ዙር ጥናቱ 2,400 ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቶች ተሳትፈዋል። በኢትዮጵያ የተቋሙ ተወካይ አቶ ሙሉ ተካ ያቀረቡት የጥናት ውጤት 61 በመቶው ኢትዮጵያዊ በድህነትውስጥ የሚኖር መሆኑን አሳይቷል።

ጥናቱ ስለ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ ምን ይላል?


የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ በዳሰሰው የጥናቱ ክፍል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ መጥፎ ብሎ ሲገልፅ፣ 64 በመቶው የጥናቱ ተሳታፉ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ መልካም ነው ማለት እንደማይችል ስለመናገሩ ታውቋል።

አፍሮ ባሮ ሜትር ኢትዮጵያ ዉስጥ ተመሳሳይ ጥናት ሲያደርግ የዘንድሮዉ ሁለተኛዉ ነዉ
ጥናቱን ያደረገዉ ተቋም እንደሚለዉ ከሁለት ዓመት በፊት በኑሮዉ ደስተኛ የነበረዉ ሕዝብ ቁጥር ዘንድሮ ቀንሷልምስል Solomon Muchie/DW

ከሁለት ዓመታት በፊት በግል ኑራቸው እርካታእንዳላቸው ገልፀው ከነበሩ 51 በመቶ ሰዎች ቁጥሩ አሽቆልቁሎ አሁን ወደ 38 በመቶ መውረዱ፣ 47 በመቶ የጥናቱ ተሳታፊዎችም የግል ኑሯቸው መልካም አለመሆኑን መግለፃቸው ተመላክቷል።

የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየት


በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የኢኮኖሚ ባለሙያእ ዶክተር አንዱዓለም ጎሹ የጥናት ውጤቱ ከነባራዊ የሀገሪቱ እውነታጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልፀዋል።በ39 የአፍሪካ ሀገሮች በዲሞክራሲ፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎች ማሕበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሕዝብን አመለካከት በዳሰሳ ጥናት የሚለካው ይህ ተቋም 18 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ በቂ ምግብ እንደማያገኝ በጥናቱ መለየቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ