1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ  እርዳታ

ረቡዕ፣ የካቲት 15 2009

የብሪታንያ ዓለም አቀፍ የልማት ጽህፈት ቤት ከአንድ ሚሊዮን የብሪታንያ ፓዉንድ በላይ ወጭ በማድረግ ለኢትዮጵያን የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረጉ እያነነጋገረ ነው።

https://p.dw.com/p/2Y4Z6
Großbritannien Theresa May vor 10 Downing Street
ምስል picture-alliance/dpa/W. Oliver

Beri London(UK trainiert Äthiopisches Sicherheitskräfte) - MP3-Stereo

 የጽህፈት ቤቱን ተግባር ዴይሊ ሜል የተባለው የብሪታንያ ጋዜጣ አሳፋሪ ሲል ወቅሷል ። ዜናው ይፋ የተደረገው 53 የብሪታንያ ምክር ቤት አባላት፣ የብሪታንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙትን ትውልደ ኢትዮጵያዊውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንዲያስፈታ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ነው ። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ድጎማ ለሰላም አስከባሪ ኅይሎች እገዛ የሚውል ነው ሲል አስተባብሏል ። 


ሐና ደምሴ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ