1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

800 ገደማ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሮም ከመኖሪያቸው ተባረዋል

ሰኞ፣ ነሐሴ 15 2009

ባለፈው ቅዳሜ የጣልያን ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ወደ 800 ገደማ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያንን በማዕከላዊ ሮም ከሚገኝ ሕንጻ አስወጥቷል። ስደተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት ጎዳና ላይ ወድቀናል፤ ፊታችንን እንኳ መታጠብ አልቻልንም ሲሉ ያማርራሉ።

https://p.dw.com/p/2ibdJ
Polizei räumt von fast 1000 Migranten besetztes Haus in Rom
ምስል picture alliance/P. Cortellessa/Pacific Press via ZUMA Wire/dpa

ከመኖሪያቸው የተባረሩት ስደተኞች

ከስደተኞቹ መካከል አንዷ የሆኑ እንስት "ቅያሬ የለንም። ልብስ አላወጣንም። ሶስት ቀን ውጭ ነው የምናድረው" ሲሉ ይናገራሉ። በድንገት ከሕንጻው እንዲወጡ መገደዳቸውንም አክለዋል። "ተጥለናል በቃ። አሁንማ ቆሻሻ ላይ ነው ያለንው" የሚሉት እኚሁ እንስት ቀጣይ እጣ ፈንታቸው ምን እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል። በሮም ከተማ ከቴርሚኒ ማዕከላዊ ባቡር ጣቢያ አጠገብ ከሚገኘው የመኖሪያ ሕንፃ ከተባሉት መካከል የሆኑ ሌላ ስደተኛ ደግሞ "ወደ አገራችን መግባት የማንችል ስደተኞች ነን። በጣም ችግረኞች ነን። አሁን ሜዳ ላይ ተጥለናል።" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከስደተኞቹ መካከል ከ200 በላይ የሚሆኑት በጎዳና እና አደባባይ ለመተኛት ተገደዋል። ሮም ስደተኞቹን ከሚኖሩበት ሕንፃ ለማስለቀቅ ወደ 500 ገደማ ፖሊሶች ማሰማራት አስፈልጓት ነበር። ዛሬ ወደ ቦታው ጎራ ብሎ የስደተኞቹን ሁኔታ የቃኘው የሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ታዝቧል።

ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ