1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የዋጋ ግሽበት

እሑድ፣ ኅዳር 10 2010

የችግሩ መንስኤ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ነው የሚሉ አሉ። መንግሥት ደግሞ ምክንያቶቹ ሰው ሰራሽ ችግሮች ናቸው ሲል ይደመጣል። ሌሎች ደግሞ ደካማ የገበያ ቁጥጥርን ለዋጋው ንረት ተጠያቂ ያደርጋሉ።

https://p.dw.com/p/2nqbt
Äthiopien Lebensmittel-Markt in Addis Ababa
ምስል DW/Y. Gebre-Egziabher

የሸቀጦች ዋጋ ንረት እና መፍትሄው

በኢትዮጵያ የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ እያሻቀበ መሄድ አሁንም በጣም አሳሳቢ እና መፍትሄ ያልተገኘለት ችግር ሆኖ ዘልቋል። በተለይ በኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ምንዛሬ ተመን ከተደነነገገ በኋላ መሠረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ብቻ ሳይሆን የተለያዩ እቃዎች ዋጋ እጅግ መናሩ ሸማቾችን ከማማረር አልፎ ግራ እያጋባ ነው። መንግሥት የየብር ምንዛሬ ዋጋ ሲቀንስ በመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ላይ ብዙም ለውጥ አያመጣም ብሎ የነበረ ቢሆንም ተመኑ ከተለወጠ ማግሥት አንስቶ በምግብ ሸቀጦች በቤት እና ቢሮ እቃዎች እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ላይ አስደንጋጭ ጭማሪ ተደርጓል። ከዋጋው መናር ሌላ የአንዳንድ መሠረታዊ ሸቀጦች እጥረትም ህብረተሰቡን እያሰቃየ ነው። በዚህ ረገድ ዋጋቸው ጣራ የነካው ስኳር እና ዘይት ተጠቃሽ ናቸው። አስተያየት ሰጭዎች የችግሩ መንስኤ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ነው ሲሉ መንግሥት ደግሞ ምክንያቶቹ ሰው ሰራሽ ችግሮች ናቸው ሲል ይደመጣል። ሌሎች ደግሞ ደካማ የገበያ ቁጥጥርን ለዋጋ ንረት ተጠያቂ ያደርጋሉ። በኢትዮጵያ የሸቀጦች ዋጋ ንረት እና መፍትሄው የዛሬ ውይይት ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ አቶ ወንድሙ ፍላቴ በኢትዮጵያ ንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ፣ አቶ ተመስገን ዘውዴ የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ እንዲሁም ዶክተር ዳንኤል ተፈራ በዩናይትድ ስቴትስ ዊስኮንሰን ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚ መምህር ተሳትፈዋል። ሙሉውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ