1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2ኛው ዙር የፈረንሳይ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2009

ፈረንሳይ ባለፈው እሁድ የሀገሪቱን ነባር ፖለቲካ የገለባበጠ የመጀመሪያ ዙር ፕሬዚደታዊ ምርጫ አከናውናለች።በምርጫዉ ነባር ፓርቲዎች ድል ተነስተው ወደ ጎን ሲገፉ፤ በፖለቲካው መድረክ ብዙም የጎላ ሚና ያልነበራቸው ፖለቲከኞች  ወደ ሁለተኛው ዙር ለማለፍ ችለዋል።

https://p.dw.com/p/2bukj
Infografik Frankreich: Mit diesen Forderungen treten die Kanditaten an Englisch

የ2ኛው ዙር የፈረንሳይ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች

ወጣቱ ፖለቲከኛ ኢማኑኤል ማክሮ በአንደኛነት፤  የቀኝ አክራሪው ብሔራዊ ግንባርን ከአባታቸው ተረክበው የሚመሩት ወይዘሮ ማሪን ለ ፔን  ሁለተኛ ኾነው ወደ ሁለተኛው ዙር ምርጫ ማለፋቸው ተዘግቧል።  ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከሪፐብሊካኖቹ የቀኝ መሀል  ወይንም ከሶሻሊስቶቹ ግራ መሀል ፓርቲዎች አንዱ እንኳን ለሁለተኛው ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማለፍ አለመቻሉ ብዙዎችን አስደምሟል። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን የሚያጠነጥነው በምርጫዉ ዉጤትና በሁለቱ መሪዎች ላይ ነው።

ገበያው ንጉሤ

ነጋሽ መሀመድ