1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመን ጦርነት፤በሽታና ረሐብ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2009

የመንን በሚያወድመዉ ጦርነት የሚፋለሙት ሳዑዲ አረቢያና ተከታዮችዋ በጦርነቱ ለሚደርሰዉ ጥፋት ተጠያቂ እንደሚሆኑ የርዳታ ርድጅት ሠራተኞች አስጠነቀቁ።የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች እንደሚሉት ጦርነቱ በቀጥታ ከፈጀዉ ሕዝብ በተጨማሪ ለረሐብና ለኮሎራ ያጋለጠዉ ሕዝብ እየሞተ ነዉ

https://p.dw.com/p/2heYk
Jemen Cholera-Ausbruch
ምስል Reuters/K. Abdullah

የመን፤ ጦርነት፤በሽታና ረሐብ

የመንን በሚያወድመዉ ጦርነት የሚፋለሙት ሳዑዲ አረቢያና ተከታዮችዋ በጦርነቱ ለሚደርሰዉ ጥፋት ተጠያቂ እንደሚሆኑ የርዳታ ርድጅት ሠራተኞች አስጠነቀቁ።የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች እንደሚሉት ጦርነቱ በቀጥታ ከፈጀዉ ሕዝብ በተጨማሪ ለረሐብና ለኮሎራ ያጋለጠዉ ሕዝብ እየሞተ ነዉ።የተባበሩት መንግሥት ድርጅት እንዳስታወቀዉ በኮሌራ በሽታ ብቻ ከሁለት ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ አልቋል።በየዕለቱ በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በበሽታዉ ይለከፋል።የርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት በሽታዉ የተከሰተዉ ሳዑዲ አረቢያ የምትመራቸዉ ሐገራት የጦር ጄቶች የቁሻሻ መተላለፊያ ቧምባዎችን፤ ሕንፃና ሆስፒታሎችን በማዉደማቸዉ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ