1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ሥጋት ተጭኖታል

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 18 2009

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መመረጥ በኋላ ከሌላው ጊዜ በከፋ ሥጋት ውስጥ ወድቋል ተባለ።

https://p.dw.com/p/2byKZ
Medienfreiheit
ምስል Getty Images/AFP/P. Lopez

ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተባለው የመገናኛ ዘዴ ነፃነት ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባ በትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና ብሪታኒያ ከአውሮጳ ኅብረት አባልነት እንድትወጣ በተደረገዉ  ዘመቻ መገናኛ ብዙኃንን የማጣጣል ተግባር ተስፋፍቷል ብሏል። ድርጅቱ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የተጀመረው ዘለፋ «አሳሳቢ ደረጃ» ላይ ደርሷል ብሏልም። የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት በስለላ እና በአምባገነን መሪዎች ተጨቁኗል ያለው ድርጅቱ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲህ የከፋ ሥጋት ውስጥ ወድቆ አያውቅም ሲል አክሏል። ዛሬ ይፋ በተደረገው ዘገባ አሜሪካ እና ብሪታኒያ ከቀድሞ ደረጃቸው አሽቆልቁለው 43ኛ እና40ኛ ደረጃ ይዘዋል። አመታዊው ዘገባ በተለይም ዴሞክራሲያዊ በሚባሉ አገሮች ፕሮፖጋንዳ እና የነፃነት ጭቆና መስፋፋቱን አትቷል። ፖላንድ እና ሐንጋሪም ትችት የጠወለገባቸው አገራት ተብለዋል። የፕሬስ ነፃነትን በማስከበር ኖርዌይ እና ፊንላድ ከአናት ተቀምጠዋል። ከ180 አገሮች ኢትዮጵያ አምና በነበረችበት 150ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ቱርክ በፕሬዝዳንቷ ሬሴብ ጣይብ ኤርዶኻን ላይ ከተሞከረው መፈንቅለ-መንግስት በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች 'ትልቅ እስር ቤት' ሆናለች ብሏል ዘገባው። ኤርትራ ደረጃዋን አሻሽላ 179ኛ ስትሆን ሰሜን ኮሪያ መጨረሻ ተቀምጣለች። 

GMF14-Partnerlogo Reporter without borders

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ