1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ስኬቶች

ማክሰኞ፣ መጋቢት 4 2010

ሜርክል ላለፉት 12 ዓመታት በሥልጣን ላይ መቆየቱ እና ለተጨማሪ አራት ዓመታት መሪ ሆኖ መቀጠሉ እንዴት ተሳካላቸው? የአሁኑ የመንግሥት ምሥረታ ረዥም ጊዜ መውሰድ በሀገር ውስጥም ሆኖ በአውሮጳ በነበራቸው ተሰሚነታቸው ላይ ተጽእኖ ይኖረው ይሆን?

https://p.dw.com/p/2uFsn
Koalitionsvertrag Unterzeichnung Koalition
ምስል picture-alliance/dpa/S. Stache

«አንጌላ ሜርክል ለአራተኛ የሥልጣን ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ»

የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ከተካሄደ ከአምስት ወር አጋማሽ በኋላ እህትማማቾቹ የክርስቲያን ዴሞክራት ህብረት እና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ ከሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ጋር ተጣምረው መንግሥት ለመመስረት የደረሱበትን ስምምነት ትናንት በፊርማቸው አጽድቀዋል። የክርስቲያን ዴሞክራቶች ህብረት ፓርቲ ሊቀመንበር ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጀርመንን ለአራተኛ የሥልጣን ዘመን ለመምራት ነገ ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሜርክል ላለፉት 12 ዓመታት በሥልጣን ላይ መቆየቱ እና ለተጨማሪ አራት ዓመታት መሪ ሆኖ መቀጠሉ እንዴት ተሳካላቸው? የአሁኑ የመንግሥት ምሥረታ ረዥም ጊዜ መውሰድ በሀገር ውስጥም ሆኖ በአውሮጳ በነበራቸው ተሰሚነታቸው ላይ ተጽእኖ ይኖረው ይሆን? የተጣማሪው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ይዞታስ እንዴት ይታያል። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ