1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኑሮ ውድነት በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 25 2015

አንድ እንጀራ የመኖሪያ መንደር ውስጥ እስከ ሃያ ብር ይሸጣል።ሽንኩርት 80፣ቲማቲም 60፣ጤፍ በኪሎ 104 ብር፣ድንች 30 ድረስ የሚሸጥባቸው ሥፍራዎች አሉ። የቤት ኪራይ በተለይ የጣራ እና ግድግዳ ግብር መንግሥት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በሚል በገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስከፈል መጀመሩን ተከትሎ ጭማሪ አሳይቷል።

https://p.dw.com/p/4Vo6H
በዚሁ የብዙዎችን ሕይወት እያከበደ በሚገኘው የኑሮ ውድነት ገዳይ ላይ የተወሰኑ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀናል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ያሻቀበው የዋጋ ግሽበት መንግሥት ሊቀለብሰው የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ደጋግመው እየገለፁ ሲሆን መፍትሔውም ሰላምና መረጋጋትን ማስጠበቅ ፣ ምርትን ማሳደግ የሚያስችለውን አማራጭ ማስፋት አድርገው ያመለክታሉ። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የኑሮ ውድነት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል። የገበያው መልክም ይሄንን ያረጋግጣል።
አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አነስተኛ የሚባል ዳቦ በአማካይ 7 ብር ይሸጣል። እስከ አስራ ሁለት ብር ድረስም የሚሸጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
አንድ እንጀራ የመኖሪያ መንደር ውስጥ እስከ ሃያ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል። ሽንኩርት 80፣ ቲማቲም 60፣ ጤፍ በኪሎ 104 ብር ፣ ድንች 30 ድረስ የሚሸጥባቸው ሥፍራዎች አሉ።
ዋነኛው የከተማው ችግር የሆነው የቤት ኪራይ በተለይ የጣራ እና ግድግዳ ግብር መንግሥት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በሚል በገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስከፈል መጀመሩን ተከትሎ ጭማሪ አሳይቷል። ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በየ ጊዜው የኪራይ ጭማሪ ማድረግን የሚከለክሉ ድንጋጌዎችን ቢያወጣም።
ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ ከአልባሳት ጀምሮ በየ ጊዜው በአስደንጋጭ ሁኔታ ዋጋቸው ይጨምራል።የኑሮ ውድነትና የህዝቡ አንገብጋቢ ጥያቄ

ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ያሻቀበው የዋጋ ግሽበት መንግሥት ሊቀለብሰው የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ደጋግመው እየገለፁ ሲሆን መፍትሔውም ሰላምና መረጋጋትን ማስጠበቅ ፣ ምርትን ማሳደግ የሚያስችለውን አማራጭ ማስፋት አድርገው ያመለክታሉ።
በዚሁ የብዙዎችን ሕይወት እያከበደ በሚገኘው የኑሮ ውድነት ገዳይ ላይ የተወሰኑ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀናል።

ስለ ኑሮ ውድነት የሰዎች  አስተያየት

" ኑሮ ከባድ ነው በአሁኑ ሰዓት። ስለ ኑሮ መወራት አይቻልም። ሰው በኑሮ በጣም ተመጣጣኝ አይደለም። ሰው ለመጠያየቅ እንኳን አልቻለም። ምን ይዤ ልሂድ እያለ ነው። አንድ ኪሎ ሙዝ ሰባ ብር በገባበት ሰዓት ፣ ዳቦ 12 ፣  ትንሽ የተባለው 7 ብር ነው። ሰላም ከመጣ ደግሞ እየተሻሻለ ሊሄድ ይችላል"።

"እንደዚህ አይነት ደረጃ ላይ መድረሳችን በርግጥ ያሳዝናል። ይህንን ደግሞ ለመቅረፍ መንግሥት የሚሰራበት ደረጃ ቢኖር ጥሩ ነው"
" እኔ ከቤተሰብ ጋር ነው የምኖረው። እንደኔ እስካሁን ብዙም አልተቸገርኩም። ኑሮ ጨመረ የሚባል አስተያየት ግን እሰማለሁ"የኑሮ ውድነት በአማራ ክልል

የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አስተያየት

"በአለም ላይ ግሽበቱ አለ። አሜሪካም ግሽበት አለ ይባላል። ግን 2 እና 3 በመቶ ሲደርስ ነው እነሱ በጣም ከባድ የሚሉት። የእኛ ግን ሁለት አሃዝ ከገባ ዘመን የለውም። ከ 30 እስከ 40 ነው በአመት ውስጥ ያለው ማለት ነው። ይሄ በጣም ከፍተኛ ነገር ነው። አሁን መንግስት ያንን ሊቀለብሰው ትክክለኛው ጊዜ አይደለም። ምክንያቱም ግጭት አለ። እርዳታ ቀንሷል።
የመጀመርያው እርምጃ ሰላምና መረጋጋትን መመለስ ይኖርበታል"።

 " ለቤት ኪራይ እርዱኝ" የሚሉ በኮምፒውተር የተፃፉ ጽሑፎችን የያዙ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች በየ ጎዳናው ይታያሉ። ፖሊስ ለልመና የሚወጡ ሰዎችን ሲያባርር እና ይህንን ድርጊት ሲከላከል ይታያል።
አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ተሽከርካሪዎች በሚቆሙባቸው አካባቢዎች ሕፃናትን ይዘው ለልመና የሚወጡ ሴቶች ማየት በብዙ እየተለመደ ነው።ምስል Alemenew Mekonnen/DW
 ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በየ ጊዜው የኪራይ ጭማሪ ማድረግን የሚከለክሉ ድንጋጌዎችን ቢያወጣም።ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ ከአልባሳት ጀምሮ በየ ጊዜው በአስደንጋጭ ሁኔታ ዋጋቸው ይጨምራል።
በክረምት በስፋት ለምግብነት የሚውለው በቆሎ እሸት እንኳን አንዱ ከ 20 ብር በታች አይገኝም።በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ማስመጣት እየተከለከለ ነው የሚሉ የተሽከርካሪ አስመጪ እና ሻጭዎች በየ ሳምንቱ በመቶ ሺህ ደረጃ ቀድመው ያስመጡት ተሽከርካሪ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ ተስተውሏል።ምስል Alemenew Mekonnen/DW

 

የተረጋጋ ገበያ እንዲሁም ግብይት አለመኖር 

አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ተሽከርካሪዎች በሚቆሙባቸው አካባቢዎች ሕፃናትን ይዘው ለልመና የሚወጡ ሴቶች ማየት በብዙ እየተለመደ ነው።
ከዚህም ሌላ " ለቤት ኪራይ እርዱኝ" የሚሉ በኮምፒውተር የተፃፉ ጽሑፎችን የያዙ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች በየ ጎዳናው ይታያሉ። ፖሊስ ለልመና የሚወጡ ሰዎችን ሲያባርር እና ይህንን ድርጊት ሲከላከል ይታያል።
በክረምት በስፋት ለምግብነት የሚውለው በቆሎ እሸት እንኳን አንዱ ከ 20 ብር በታች አይገኝም።
በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ማስመጣት እየተከለከለ ነው የሚሉ የተሽከርካሪ አስመጪ እና ሻጭዎች በየ ሳምንቱ በመቶ ሺህ ደረጃ ቀድመው ያስመጡት ተሽከርካሪ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ ተስተውሏል።
በከተማእ ምንም እንኳን ብዙ ቤት እልሚዎች ገበያውን እየተቀላቀሉ ቢሆንም ቤቶች ገና ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ በካሬ ሜትር የሚሸጡበት ዋጋ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ በየ ወሩ ብቻ ሳይሆን በየ ሳምንቱ ጭምር እየተለዋወጠ ገበያው መረጋጋት ያጠረው ሆኗል።የኑሮ ውድነት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል
መንግሥት ከፍተኛ ድጎማ ያደርግበት የነበረውን ነዳጅ ቀስ በቀስ ድጎማውን እየቀነሰ በመምጣቱ ትናንት እንኳን ከአንድ ሊትር ነዳጅ ላይ የ 7 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።ይህ የኑሮ ውድነቱን የበለጠ እንዳያባብስ ያሰጋል።
በዓመቱ መጨረሻ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዩ ዓመት 7.5 በመቶ እንደሚያድግ ሆኖም የዋጋ ግሽበትና ንረት እንደ መከራ የተስፋፋ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በየ ጊዜው የኪራይ ጭማሪ ማድረግን የሚከለክሉ ድንጋጌዎችን ቢያወጣም።ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ ከአልባሳት ጀምሮ በየ ጊዜው በአስደንጋጭ ሁኔታ ዋጋቸው ይጨምራል።
ዋነኛው የከተማው ችግር የሆነው የቤት ኪራይ በተለይ የጣራ እና ግድግዳ ግብር መንግሥት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በሚል በገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስከፈል መጀመሩን ተከትሎ ጭማሪ አሳይቷል። ምስል Seyoum Getu/DW

ሰሎሞን ሙጬ 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ