1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን

እሑድ፣ ነሐሴ 21 2015

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?

https://p.dw.com/p/4VayN
የፋኖ ታጣቂ፦ አማራ ክልል ላሊበላ። ፎቶ ከማኅደር
በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች ተደጋጋሚ ውጊያዎች እና ግጭቶች ከተከሰተባቸው ቦታዎች አንዷ ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ናት ። የፋኖ ታጣቂ፦ አማራ ክልል ላሊበላ። ፎቶ ከማኅደርምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

የግጭቱ አዘጋገብ ምን ይመስላል?

በኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ አንዱ ግጭት ጋብ አለ ሲባል ሌላ ግጭት እና የፖለቲካ መቧደን እየተፈጠረ ሁኔታው እንደ አዙሪት መሽከርከሩን ቀጥሏል ። ባለፈው የሰሜን ኢትዮጵያግጭት በትግራይ፤ አማራ እና አፋር ክልሎች የደረሰው ሞት ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና እጅግ ብርቱ የንብረት ውድመት ጠባሳው ገና ሳይጠግግ፤ ወደ ሌላ ግጭት እና ሌላ የፖለቲካ መቧደን እየተስተዋለ ነው ።

የአማራ ተወላጆች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸውም ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለእኛም የደረሰን መልእክት አለ ። በእርግጥ እስራቱበጅምላ መሆኑ ተለየ እንጂ በርካታ የማኅበረሰብ አንቂዎች፤ ጋዜጠኞች ፤ የመገናኛ አውታር ባለሞያዎች እና ፖለቲከኞች በቅርቡ የአማራ ክልል ክልል ግጭትን ተከትሎ ለተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፊትም ሆነ በኋላ ለእስር መዳረጋቸው ተዘግቧል ።

የፕሬስ ነጻነት ምልክት። ፎቶ ከማኅደር
በኢትዮጵያ ግጭት እስር ግድያውን በአግባቡ አልተዘገበም የሚሉ አሉ ። የተለያዩ የመገናኛ አውታር ባለሞያዎች መታሰራቸው፤ በአንዳንድ አካባቢዎችየኢንተርኔት ገደብ በነጻነት ለመዘገብ እክል መሆናቸው ይጠቀሳል ። የፕሬስ ነጻነት ምልክት። ፎቶ ከማኅደር ምስል Yaghobzadeh Alfred/ABACA/picture alliance

ለመሆኑ ይህ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገራት የዴሞክራሲ እና የመብት ተቆርቋሪዎች ብሎም የመገናኛ አውታሮች ዘንድ ምን ያህል የሚገባውን ሽፋን አገኘ?  የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን የእንወያይ መሰናዶ የሚያተኩርበት ርእሰ ጉዳይ ነው።  በውይይቱ 3 እንግዶች ተሳታፊ ናቸው ። 

በዚህ ውይይት ከመንግስት በኩል ተሳታፊ እንዲመደብልን ለጠቅላይ ሚንሥትር ጽ/ቤት፤ እንዲሁም በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሚመለከታቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት በይፋዊ የኢሜል መልእክት ጠይቀን ነበር ። ውይይቱን እስካከናወንንበት እስከ ሐሙስ አመሻሹ ድረስ ግን ከአንዳቸውም ምላሽ አላገኘንም ።  ሁለት ምሑራንም አንዱ ከኢትዮጵያ ሌላኛው ከዩናትድ ስቴትስ በውይይቱ ለመሳተፍ ፈቃደኛነታቸውን ከገለጹ በኋላ በውይይቱ ቀን ስልካቸውን አላነሱም ።ሦስቱ ተወያዮች ግን ጥልቅ ውይይት አድርገዋል ።

ሙሉውን ውይይት ከድምጽ ማእቀፉ ማግኘት ይቻላል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ