1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለወላዶች በነጻ አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር

ማክሰኞ፣ መጋቢት 25 2010

በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ዘንድ የመውለጃ ጊዜአቸው የተቃረበ ነፍሰ ጡሮችን ያለምንም ክፍያ ወደ ህክምና ተቋማት ስለሚያደርሱ አሽከርካሪዎች የሚያወሱ ጽሁፎች እና ፎቶዎች ተወዳጅነትን አትርፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ “ላዳ” ታክሲ የሚያሽከረክረው ቴዎድሮስ አቦሃይም ተመሳሳይ መልካም ተግባሩ በብዙዎች አስመስግኖታል።

https://p.dw.com/p/2vQba
Tewodros Abuhay
ምስል DW/Yohannes G/Egziabher

ለወላዶች በነጻ አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር

በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ዘንድ የመውለጃ ጊዜአቸው የተቃረበ ነፍሰ ጡሮችን ያለምንም ክፍያ ወደ ህክምና ተቋማት ስለሚያደርሱ አሽከርካሪዎች የሚያወሱ ጽሁፎች እና ፎቶዎች ተወዳጅነትን አትርፈዋል፡፡ የአሽከርካሪዎቹ መልካም ተግባር በብዙዎች ተወድሷል፡፡ ከዚህ ቀደም በጎንደር ያለ የባጃጅ አሽከርካሪ ተመሳሳይ ታሪክም በዚሁ በዶይቼ ቬለ መስተናገዱ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ እንወስዳችኋለን፡፡ በተለምዶ “ላዳ” ተብሎ የሚጠራውን የኮንትራት ታክሲ የሚያሽከርክር አንድ ወጣት የሚፈጽማቸውን ሰብዓዊ ተግባራት እናስተዋውቃችኋለን፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን የዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ጥንቅር ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡ 

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ