1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ምስረታ 60ኛ ዓመት

ዓርብ፣ መጋቢት 15 2009

የአዉሮጳ ኅብረትን እዉን ያደረገዉ የሮማዉ ስምምነት 60 ኛ ዓመት ስምምነት ነገ በሮማ ኢጣልያ በሚደረጉ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል። ዛሬ በዋዜማዉ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስቴርና የአዉሮጳ ኅብረት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች የሠራተኞችና የንግድ ማኅበራት ሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/2ZtDl
Deutsches Logo zum EU-Jubiläum 2007

Ber. Brüssel(60 Jahre Römische Verträge und der Marsch für Europa II) - MP3-Stereo


የኅብረቱ መሪዎች ማምሻዉን ከሮማዉ ርዕሰ ሊቃነ- ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር እንደሚገናኙ ታዉቋል። በነገዉ እለት 27 ቱ የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች ተሰብስበዉ  ኅብረቱ የ 60 ዓመት ጉዞና ያገጠሙትን ተግዳሮቶች በመገምገም የወደፊቱን የጉዞ አቅጣጫና ግብ የሚያሳይ አዲስ ሰነድ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከመሪዎቹ ስብሰባ በተጓዳኝ የኅብረቱ ደጋፊ ኃይሎች የጠሩት ታላቅ አዉሮጳ አቀፍ የድጋፍ ሰልፍም በሮማ አደባባዮች ይደረጋል። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።

 

ገበያዉ ንጉሤ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ