1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እርዳታ ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት

ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010

ውሳኔው በተለይ ከአውሮጳ ህብረት ውጭ በአስቸኳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን እና የትምሕርት እድል የተነፈጋቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን ለመርዳት የሚያስችል ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/2y4K8
EU Kommissar Christos Stylanides
ምስል DW/A. De Loore

የአውሮጳ ህብረት እና የትምሕርት መ/ግብሮች

የአውሮጳ ሕብረት ግጭት እና የፖለቲካ ቀውስ ባሉባቸው አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብሮችን ለማጠናከር እና ለማስፋት ማቀዱን አስታወቀ። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከመጪው የጎርጎሮሳዊው 2019 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ከሰብዓዊ እርዳታ ጠቅላላ በጀቱ 10 በመቶው ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብር እንዲውል ተወስኗል። ውሳኔው በተለይ ከአውሮጳ ሕብረት ውጭ በአስቸኳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን እና የትምሕርት ዕድል የተነፈጋቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ለመርዳት የሚያስችል ነው ተብሏል። 

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ