1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባው ሰልፍ ዝግጅት

ዓርብ፣ ሰኔ 15 2010

ነገ አዲስ አበባ በአይነቱ ለየት ያለ ሕዝባዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች። መስቀል አደባባይ እስከዛሬ ያስተናገደው የሰልፍ አይነት አንድም በመንግሥት ተቀስቅሶ ለድጋፍ የወጣ ሰልፈኛ አንድም አሁን ተፎካካሪ በሚል ስያሜያቸው በተቀየረላቸው የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ በመንግሥት ይፈጸማል የሚለውን ለመቃወም የወጣ ተሰላፊን ነበር።

https://p.dw.com/p/3071w
Äthiopien Vorbereitungen zur Kundgebung im Unterstützung zum Premierminister Abiy
ምስል DW/Y. Gebregziabeher

ከሦስት እስከ አራት ሚሊየን ሕዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

 የነገው ሰልፍ አስተባባሪዎች መደመርን እያቀነቀኑ አንዱ ሌላውን በፍቅር እና ይቅርታ እያየ ምስጋና እና አብሮነቱን እንዲገልፅበት መድከማቸውን ይናገራሉ። ዕለቱንም የምስጋና ቀን ብለውታል። ከሦስት እስከ አራት ሚሊየን ይገኝበታል በተባለው ሰልፍ ሁሉም መስቀል አደባባይ ተገኝቶ መታደም ስለማይችልም በየቦታው ስክሪን እንደሚሰቀልም ጠቁመዋል። ባጠቃላይ ዝግጅቱ ከምን ደርሷል? የሕዝቡስ ስሜት? አዲስ አበባን ተዘዋውሮ የቃኘው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዛሬ አስተባባሪዎቹ መግለጫ ሲሰጡም ተገኝቶ ነበር። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ጠይቄው ነበር። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ