1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባው ጥቃት በጠቅላይ ምኒስትሩ ላይ ያነጣጠረ ነበር- የሰልፉ አዘጋጆች

እሑድ፣ ሰኔ 17 2010

በትናንትናው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በጠቅላይ ምኒስትር አብይ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አዘጋጆቹ ተናገሩ። ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምኒስትሩ ንግግራቸውን ጨርሰው በመሰናበት ላይ ሳሉ ግርግር ተጀምሮ ከዚያ ፍንዳታው ተከትሏል።

https://p.dw.com/p/30BvI
Äthiopien, Addis Abeba Pro PM Versammlung Pressekonferenz
ምስል DW/Y.Geberegziabher

የአዘጋጆች ጋዜጣዊ መግለጫ

በትናንትናው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተጸመው ጥቃት በጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አዘጋጆቹ ተናገሩ። ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምኒስትሩ ንግግራቸውን ጨርሰው በመሰናበት ላይ ሳሉ ግርግር ተጀምሮ ከዚያ ፍንዳታው ተከትሏል። አዘጋጆቹ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ደም እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፉ መንፈስ ፤ ይተላለፉ የነበሩ መልዕክቶች እንዲሁም ጠቅላይ ምኒስትሩ ያደረጉት ንግግር ስለ አገር እንድነት የሚሰብኩ መሆናቸው መልካም እንደነበር ገልጸዋል። ለዶይቼ ቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በስተኋላ የተፈጸመውን ጥቃት አጥብቀው ኮንነዋል።

ሙሉ ዘገባው የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር