1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግስት የ2009 ዓ.ም በጀት

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ሰኔ 28 2008

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለ2009 ዓም ዛሬ ካፀደቀው 274,3 ብሊዮን ብር በጀት በጀት ለካፒታል ወጭ 105,7 ብሊዮን ብር፣ ለክልሎች የምሰጥ ድጋፍ 87,8 ብሊዮን ብር፣ ለመደበኛ ወጭ 68,8 ብልዮን ብር እንዲሁም 12 ብልዮን ብር ለሌሎች ልማት ማስፈፀምያ መመደቡም የመንግስት መገናና ብዙሃን ኢየዘገቡ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1JJVb
Äthiopien Kabinett
ምስል DW/G. Tedla HG

[No title]

እንደ ዘገባዉ ከሆነ ለክልሎችም ከተደለደለዉ በጀት ኦሮሚያ 28,5 ቢሊዮን ብር፣ አማራ 20,4 ቢሊየን ብር፣ እና ደቡብ ክልል 17,7 ቢሊየን ብር ተመድቦላቸዋል ። እነዚህ ክልሎችም ከበጀቱ ከፍተኛ ድርሻ ሲይዙ፣ ሶማሌ 7,1፣ ትግራይ 6,3 ቢሊየን ብር፣ አፋር 2,7 ቢሊየን ብር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 1,9 ቢሊየን ብር፣ ጋምቤላ 1,3 ቢሊየን ብር፣ ድሬዳዋ 1 ቢሊየን ብር እና ሀረሪ 876,6 ሚሊየን እንደሚከፋፈሉም ዘገባዉ ያትታል።


ባለፈዉ አመት ከተመደበዉ 233,3 ቢልዮን ብር የዚህ ዓመት በጀት በ41 ቢልዮን ብር መጨመሩ ይታወቃል።
ለአንድ አገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ ጠንካራ የብሄራዊ ቁጠባ ወሳኝ መሆኑን እና ከአገር ዉስጥ ከግብርም ሆነ ግብር ካልሆኑ ምንጮች ከሚገኙ ገቢዎች በጀቱን መበጀት መቻልም አስፈላጊ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።


ባለፈዉ ዓመት ከተመደበዉ 233,3 ብሊዮን ብር 16 በመቶዉ በዉጭ ብድር እንዲሁም ከቀረው አብዛኛው ከሃገር ዉስጥ ምንጮች እንደምሸፍን ተዘግቦ ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ጌታቸዉ ተክለማርያም አገርቱ ከዉጭም ሆነ ከሃገር ዉስጥ የምትበደረዉ ገንዘብ ኢየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው መንግስት ከአገር ዉስጥ፣ በተለይም ከብሄራዊ ባንክ የሚበደር ከሆነ ከንዘብ አትሞ ወደ ገበያዉ ስለሚያስገባ የዋጋ ግሸበት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ይናገራሉ።


በዶቼ ቬሌ ድረ ገፅ ላይ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከተሰጡት አስተያየቶች ዉስጥ አገሪቱ የተመደበዉን በጀት በስነ ስርዓት ከተጠቀምች ኢኮኖሚዋን እንደምያረጋጋ እና ለካፒታል ወጭዎች ከሃገር ዉስጥ ብትበደር የዉጭ ዕዳም ሆነ የዋጋ ግሸበቱን የመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለዉ የጠቆሙት ይገኙበታል።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ