1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ግንቦት 2 2009

በኢትዮጵያ የነበረዉ ከፍተኛ ተቃዉሞን ተከትሎ መንግስት በመስከረም ወር 2009 ዓ/ም ለስድስት ወር የሚዘልቅ የአስቸኴይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። የአዋጁ አስፈላጊነትና የታለመዉን ሰላምና ማረጋጋት ማስፈኑ ወይም አለማስፈኑ አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥለዋል።

https://p.dw.com/p/2chKA
Karte Äthiopien englisch

mmt Ethiopia's State of Emergency - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት ወር 2009 ዓ/ም ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለቀጣይ አራት ወራት እንዲራዘም ማድረጉ ይታወቃል። የአዋጁ አስፈላጊነትና የታለመዉን ሰላምና ማረጋጋት ማስፈኑ ወይም አለማስፈኑ አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት አዋጁ በከፊል ሰላምንና መረጋጋትን መልሰዋል ሲልም ይደመጣል። ይሁን እንጅ ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የመንግስትን አባባል አይቀበሉትም። መጀመርያዉኑ አዋጁ «ሕገ-መንግስቱን የጣሰና ዜጎችን የማያንቀሳቅስ» ሆኖ አግኝቸዋለሁ የሚሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ መንግስት ሕዝቡን አረጋግቻለዉ የሚለዉ «ፍፁም ከእዉነት የራቀ ነዉ» ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረውል። ምክንያቱ ደግሞ ይላሉ አቶ የሽዋስ አባሎቻችን ያለምክንያት እየታሰሩ ይገኛሉ።

በአገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ቦንብ መፈንዳት ሁኔታ የምንሰማበት ወቅት ላይ ነዉ አሁን ያለነዉ የሚሉት አቶ የሽዋስ ኦሮሚያም ሆነ አማራ ክልል አሁንም በወታደራዊ አገዛዝ ስር ይገኛሉ ብለዋል። 

ነዋሪዉ ማኅበረሰብስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተደነገገበት ባለፉት ሰባት ወራቶች በአካባቢዉ አለ የሚባለዉን ሰላምና መረጋጋት እንዴት ይመለከተዋል?

ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአዳማ ነዋሪ እንደገለፁት መንግስትን የተቀየመዉ ማኅበረሰብ በመልካም አስተዳደር ችግርም ሆነ የስራ እድል መፍጠሩ ረገድ ላይ ከመንግስት ጋር ያለዉ እንቅስቃሴ የጎላ አይደለም ብለዋል። ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ ግን አልተሳካም። 
 

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ