1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር አባላት ምርጫ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 30 2010

10ኛው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባዔ የፌደሬሽኑ ፕሬዚደንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ እንዲራዘም ወሰነ። ምርጫው የተራዘመው የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ ፊፋ ሕጎች በመጣሳቸው መሆኑ በይፋ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/2nMkS
FIFA Logo
ምስል Reuters/R. Sprich

«ተመራጮች ከሙያው ጋር ቅርበት ያላቸው መሆን አለባቸው።»

ተጣሱ ከተባሉት ሕጎች መካከል የክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ መስተዳድሮች የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ምን ያህል ተፎካካሪ ይልካሉ በሚለው ጉዳይ ላይ ከሀገር አቀፉ ፌዴሬሽን ጋር የተፈጠረው ልዩነት ይጠቀሳል። ይህ በዚህ እንዳለ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በሌሎች የስፖርት ፌዴሬሽኖች ውስጥ የሚቀመጡ የአመራር አባላት ለሙያው ቅርበት የሌላቸው መሆኑ ስፖርቱን ጎድቶታል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ተንታኞች ተችተዋል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ነሀሽ መሀመድ