1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የኢትዮጵያ እና የግብፅ ግንኙነት 

ሐሙስ፣ ጥር 10 2010

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የመሩት የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እና የግብፅ አቻዎቹ የሁለቱን ሐገራት ስድስተኛ የጋራ ኮሚሽን ሥብሰባ ካይሮ ግብፅ ዉስጥ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/2r76i
Ägypten Kairo Nil-Fluss
ምስል Imago/Zumapress

ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተም ተወያይተዋል፤

 ትናንት ካይሮ የገባዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታ አልሲሲ ከመሩት ከግብፅ አቻዎቹ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።የሁለቱ መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ካይሮ ዉስጥ የተሰበሰቡት ኢትዮጵያ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰበብ የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት መሻከሩ በሚነገርበት ወቅት ነዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንዳሉት ግን ያሁኑ ጉብኝትና ስምምነት የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት ከአባይ ያለፈ ግንኙነት እንዳላቸዉ የሚያረጋግጥ ነዉ።አቶ መለስን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግራቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ