1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሰላም ተስፋ

ሐሙስ፣ ሰኔ 14 2010

ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ እንዳስታወቁት መንግሥታቸዉ ጉዳዩን የሚያጠና የመልዕክተኞች ጓድ ወደ አዲስ አበባ ይልካል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባንፃሩ የኤርትራ መንግሥትን ምላሽ በበጎ መልኩ እንደሚቀበለዉ አስታዉቋል

https://p.dw.com/p/2zx9g
Eritrea Präsident Isaias Afwerki
ምስል Eritrea Minister of Information/Y.G. Meskel

(Q&A) EMoF Reax on Ertitrea - MP3-Stereo

ኤርትራ ዝምታዋን ሰበረች።የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራን የድንበር ዉዝግብ ያስወግዳል የተባለዉን ሥምምነት እና ዉሳኔን ኢትዮጵያ ገቢር እንደሚያደርግ ካሳወቀ ሁለት ሳምንት ደፈነ።በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ሳይሰጥ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረዉ የኤርትራ መንግስት ዛሬ ለኢትዮጵያ ጥሪ ቀና መልስ የሰጠ መስሏል።የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ እንዳስታወቁት መንግሥታቸዉ ጉዳዩን የሚያጠና የመልዕክተኞች ጓድ ወደ አዲስ አበባ ይልካል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባንፃሩ የኤርትራ መንግሥትን ምላሽ በበጎ መልኩ እንደሚቀበለዉ አስታዉቋል።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንዳሉት  የኤርትራ መንግስት መልስ ለሁለቱ ሐገራት ግንኙነት መሻሻል ብቻ ሳይሆን ለቀጠናዉም ሠላም ጠቃሚ ነዉ።አቶ መለስን፤ ተስፋዓለም ወልደየስ አነጋግሯቸዋል።

ተስፋዓለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ