1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር መረራ የእስር ሁኔታን በመቃወም አቤቱታ መቅረቡ 

ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 2010

በእስር ላይ የሚገኙት  የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ ኦፌኮ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ፣ ጉዳያቸው በታየበት በዚህ ሳምንት ሰኞ ፍርድ ቤት የተወሰዱት እጃቸው በብረት ታስሮ እንደነበረ ከጠበቆቻቸው አንዱ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2m6R8
Äthiopien  Dr Mererra & Medrek
ምስል DW/Yohannes G. Egziabher

የዶክተር መረራ የእስር ሁኔታ

አቶ ወንድሙ ለዶይቸ ቬለ እንዳስረዱት፣ ይህ ዓይነቱ አሰራር ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የሞራል ድጋፍ የለውም። በዶክተር መረራ ጤንነት ላይም አሳሳቢ መዘዝ ሊያስከትል ስለሚችል ተቃውሟቸውን፣ እንዲሁም፣ ሌሎቹ ጠበቆቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ወዳጆቻቸው እንዳይጎበኙዋቸው ያረፈው እገዳ እንዲነሳ በመጠየቅ ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አቤቱታ አቅርበዋል።


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ