1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ተጣማሪ ፓርቲዎች ፈተና

ማክሰኞ፣ ጥር 8 2010

ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸዉ ሁለቱ የጀርመን ትላልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የክርስቲያን ዴሞክራቶቹ ሕብረት (CDU) እና የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ (SPD) ተጣማሪ መንግሥት ለመመስረት በቅርቡ ያደረጉት ጊዚያዊ ዉልና በጋራ ያወጡት ሰነድ አዲስ  ዉዝግብ ቀስቅሷል።

https://p.dw.com/p/2qwY2
Deutschland Berlin - Angela Merkel
ምስል Getty Images/AFP/T. Schwarz

በጀርመን የትልቁ ጥምረት ዉዝግብ

የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ ሰነዱ እንዲሻሻል ሲጠይቅ፤ የክርስቲያን ዴሞክራቶቹ ሕብረት ግን በሰነዱ ላይ «የሚጨመርም የሚቀነስም የለም» ባይ ነዉ።ሠነዱ የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መሪዎች እና አባላትንም እያወዛገበ ነዉ። ሰወስት መልክ የያዘዉ ዉዝግብ የጀርመንን የመንግሥት ምሥረታ እና የሁለቱን  የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችን ሥልጣን ላደጋ ሊያጋልጠዉ ይችላል እየተባለ ነዉ።የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን የዉዝግቡን ምክንያት እና ደረጃ ይቃኛል።የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ