1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማክሮ ቃለ መጠይቅ

ሐሙስ፣ ግንቦት 2 2010

ጀርመንን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ አሁን አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የአሜሪካን ከኢራን የኒዩክልየር ስምምነት መውጣት እና ስለሌሎችም የአውሮጳ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከዶይቸ ቬለ እና ከጀርመኑ ARD ከተባለ ቴሌቪዥን ጋር ትናንት ረዘም ያለ ቃለ ምልልስም አድርገዋል። 

https://p.dw.com/p/2xV91
Karlspreis 2018 zu Aachen | Emmanuel Macron, Präsident Frankreich | DW-Interview
ምስል DW/B. Riegert

ኢማኑዌል ማክሮ

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ በአሁኑ ሰዓት ትልቁን ቦታ ስለያዘው ስለ ኢራን የኒዩክልየር ውል በቃለ-ምልልሳቸው ላይ አንስተዋል፡፡

„…ዉሉን አስመልክተው የአሜሪካን ፕሬዚዳንት የወሰዱት ውሳኔ ያሳዝናል፡፡በእኔ ዕምነት እንደዚህ ዓይነቱን እርምጃ በአሁኑ ሰዓት መውስድ ስህተት ነው፡፡ ስለዚህ እኛ አውሮጶች አንድ ላይ ቆመን ፣ከኢራን ጋር የተደረሰበትን ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ ይኖርብናል፡፡“

ከጣቢያችን ከዶቸ ቬለ እና ከሌላው ከጀርመኑ ቴሌቪዥን ታቢያ ከ ኤ አር ዲ ጋር ከመነጋገራቸው በፊት ፕሬዚዳንቱ ይህኑን ጉዳይ አስመልክተው፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት ከ ሚስተር ሓሳን ሮሓኒ ጋርም በስልክ እንደተነጋገሩ፣እግረ መንገዳቸውን ጠቅሰው አልፈዋል፡፡

በንግግራቸውም ላይ የአውሮጳ ህብረትን አቋም ለፕሬዚዳንቱ ለሓሳን ሮሃኒ መልስው ግልጽ እንዳደረጉላቸው ተናግረዋል። አያይዘውም „….በአሜሪካ ጉብኝቴ ፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከኢራን መንግሥት ጋር በስንት መከራ ማሠሪያ ያገኘውን ውል ውድቅ እንዳያደርጉት እና እንዳይሽሩት እሳቸውን ለማሳመን ብዙ ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ ይህ ግን አልተቻለም፡፡አሜሪካኖች አንቀበለውም ስለአሉ እኛ የተቀረነው -መንግሥታት- ጠቅላላውን ስምምነት ውድቅ ማድረግ የለብንም፡፡እንዲያውም በአዳዲስ ሓሳቦች ፣ውሉን አናሻሽላለን ከ2025 ዓ.ም. እ.አ.አ.“…ከዚያ አልፎ የሚሄድ የጋራ ሰነድ ከኢራን ጋር አብረን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡“

Karlspreis 2018 zu Aachen | Emmanuel Macron, Präsident Frankreich | DW-Interview
ምስል DW/B. Riegert

ሃያ ደቂቃ በፈጀው ቃለ-ምልልሳቸውም ላይ ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት አውሮጳ ከዩናይትድ እስቴት ኦፍ አሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት „…በቀውስና በቸግር ላይ  ብቻ“የተወጠረም አይደልም“ 

„….በመካከላችን አለመግባባት አለ፡፡በዚያውም መጠን ደግሞ በአውሮጳና በአሜሪካ መካከል የቆየና እና በብዙ መንገዶች የተፈተነ ጠንካራ ግንኙነትም ፣በሁለታችን መካከል አለ፡፡ የዓለም ፀጥታ እንዳይናጋ ሽብር ፈጣሪዎችን በጋራ በመዋጋት ላይ -በሶሪያና በአፍሪካ ይህ ይታያል - አንድ ዓይነት የጋራ አቋም፣በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል አለ፡፡ግን ደግሞ በእኔ አስተሳሰብ ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስንት ጥረትና ትግል የተዘረጉት የጋራ ስምምነቶችና ውሎች አሁን አደጋ ላይ ወድቀዋል..፡፡“ እነሱም እንዳይናጉ አውሮጶች የግድ አንድ ላይ ሁነው - እነዚህን ውሎች እና ሰምምነቶች መጠበቅም“ ይኖርባቸዋል፡፡»

Karlspreis 2018 zu Aachen | Emmanuel Macron, Präsident Frankreich | DW-Interview
ምስል DW/B. Riegert

በዚህም አመለካከታቸው  ማክሮን የአሜሪካን መንግሥት በአውሮጳ የእንዱስትሪ ምርቶች ላይ የቀረጥ ክፍያውን ከፍ ለማድረግ ማቀዱን አያይዘው ተችተዋል፡፡ ስለ አውሮጳ ውስጣዊ ችግሮችም አንስተዋል፡፡

«ብዙ አባል አገራት በአሁኑ ሰዓት ኃይለኛ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ናቸው የሚባለትን የአውሮጳ ውስጣዊ ሁኔታን አሻሽሎ ማሕበረሰቡን ለማጠናከር“ -ፕሬዚዳንት ማክሮን- „…በርካታ የማሻሻያ ሓሳቦችን“ ለጀርመን ቻንሰለር፣ ለወይዘሮ አንጌላ ሜርክል .ቀደም ሲል መልስ እንዲሰጡበት መልዕክታቸውን ልከው ነበር፡፡

„መልስ በጊዜው በአለማግኛታቸውም“ እሳቸው „እንደ አልተገረሙ“ ጠቅሰዋል፡፡

“እኛ ላቀረብናቸው ሓሳቦች ፣ጀርመኖች እስከ ሰኔ ድረስ መልስ ይዘው ይቀርባሉ፡፡በርካታ አጥጋቢ መልሶችም እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከቻንስለሩዋና ከጣምራ መንግሥታቸው ብዙ ነገሮችን እጠብቃለሁ፡፡ በጋራም ሆነን፣ሁለታችን ጠንካራዋን እና አንድ የሆነችውን እንዲሁም ብሔራዊ ነጻነትዋ የተጠበቀውን አውሮጳን፣በጋራ እንደምንገነባም ትልቅ ተስፋ አለኝ“ ብለው ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ቃለ-ምልልሱን አጠናቀዋል፡፡

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ