1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
7 ምስሎች
Merga Yonas Bulaዓርብ፣ ጥር 27 2008
https://p.dw.com/p/1HqC5


ዉሃን መጠባበቅ
ኮንቴኔሮቹ ባዶ ናቸዉ፣ ንፁ ዉሃ በአከባቢዉ አይታይም። ለወራቶች በኢትዮጲያ ዝናብ አልዘነበም። በአሁኑ ሰዓት በዚሕ አከባቢ ያሉት ሰዎች በ30 ዓመት ዉስጥ ለመጀመርያ ነዉ የተባለ አስከፊ ድርቅ አገጥመቸዋል። እንደ ተባበሩት መንግስታት ከ10 ምሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደምያስፈልጋቸዉ እና እሄም ከጥቂት ጊዜ በዋላ ከእጥፍ በላይ እንደሚሆን ነዉ። በሌሎች አፍርቃ አገሮችም ይህ ሁኔታ አስፈሪ ሆኖዋል።


ከባድ ጥቃት
አብዛኛዉ ኢትዮጲያዉያን የሚኖሩት በግብርና እና በቤት እንስሳት ዉጤቶች ነዉ። ብዙ ግዜ የራስ የሆነ የቤት እንስሳት መኖር ማለት ለአብዛኛዉ ቤተሰብ መኖርን ያረጋግጣል። «የመጨረሻዉ ዝናብ የጣለዉ ባሳለፍነዉ ረመዳን ወር ነበር» ሲል በአፋር ክልል የሚኖር አንድ አርሶአደር ተናግሯል። <<ከዛን ግዜ ጀምሮ ዝናብ አልዘነበም። ዉሃም የለም፣ ሳርም የለም። ከብቶቻችንም ዝም ብሎ እየሞቱብን ነዉ።>>



ለልጆች አስጊ
ድርቅና ረሃቡ የ1984ቱ ትዉስታ ነዉ፣ በዚያን ግዜ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ባስከተለዉ ሕመም ህወታቸዉ አልፈዋል። አሁንም አገርቱ ቀጣዩ የረሃብ ቀዉስ መሃል ትገኛለች። በተለይም ሕፃናቶች በዚህ እንደሚጠቁ ነዉ። እንደ ኢትዮጲያ መንግስት ከ400,000 በላይ ሰዎች በሃይለኛ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግር እንዳጋጠማቸዉ እና እነሱም ህክምና እንደምያስፈልጋቸዉ ነዉ።



የኤልኒኖ ሙቅ ትንፋሽ
በዝምባቡዌ አዝመራዉ ትንሽ ነዉ። ይልቁንስ በሃራሬ ከተማ አካባቢ የሚገኙት ማሳዎች የሚያበቅሉት የደረቀ በቆሎዎች ናቸዉ። ለዚህም መንሴ የሆነዉ የኤልኒኖ የአየር ጠባይ በመከሰቱ ሲሆን፣ በዚህን ግዜ ካልተጠበቀ በላይ ጠንካራ በመሆኑ ነዉ። ይህም ያስከተለዉ እንደ ዝንባቡዌ ያለዉ አስከፊ ድርቅ እና ጎርፍ በለሎች አለም ክፍሎች ነዉ።



በመጨረሻዉ ጉልበት
ሙሉ በሙሉ የደከመች ከብት በእግሯ መቆም አትችልም። በማዕከላዊ ዝምባቡዌ፣ በማስቭንጎ፣ የሚገኙ አርሶአደሮች ከብቶቹ እንዲንቀሳቀሱ ይሞክራሉ። በጎርጎሪያኑ 2015 የዘነበዉ ዝናብ ከበፊቱ ግማሹ ነዉ ፣ ማሳዎች እና የግጦሽ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ደርቀዋል።


በደረቁ መሬት ላይ
በጥቁሩ ኡምፎሊዝ ወንዝ ምክንያት በአብዛኛዉ ግዜ አንድ ሰዉ በዝህ ግዜ መቆምም ሆነ መቀመጥ አይችልም። ይሁን እንጅ በሴሜንምስራቅ ደቡብ አፍርቃ የምገኘዉ ይህ ወንዝ አሁን ደርቀዋል። ወንዙ የነበረበት መሃሉ ላይ የዉሃ ጉድጓድ ስለተቆፈረላቸዉ አሁን ህብረተሰቡ ዉሃ ከዛ ያገኛሉ።


ድርቁ ዋጋ አንሮታል
ማላዊም በአስከፊ ድርቅ ተጠቅታለች። ህብረተሰቡ ይህን በዋና ከተማዋ ሊሎንጉዌ ቅርብ ያለዉ ገበያ እንደሰማዉ አድርጎታል፤ ምክንያቱም የምግብ ዋጋ እንደነ ቦቆሎ ያሉት በከፍተኛ ዋጋ በመጨመራቸዉ ነዉ። ይህም ሊሆን የቻለዉ እዝመራዉ ጥሩ ስላልነበረ እና ምግቦች ከዉጭ ስለሚገቡ ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ ደሃዉ ህብረተሰብ ይህን ለመግዛት አቅም የለዉም።