1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይን በመደገፍ የሚካሄድ ሰልፍ

ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2010

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድን እና አመራራቸውን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን ቅዳሜ ለማድረግ መታቀዱ ተገለጸ። በራስ ተነሳሽነት የተደራጁ ስድስት አባላት ያሉት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለው፣ የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሰልፍ ለጠ/ሚንስትሩ እስካሁን ላደረጉት ሁሉ ምሥጋና የሚቀርብበት ይሆናል።

https://p.dw.com/p/2zrfa
PK in Addis Abeba Elelle Hotel
ምስል DW/Y. Gebregziabeher

«የየትኛውም ፓርቲ አጀንዳም ሆነ የዘር፣ የሀይማኖት አስተሳሰብ የማይንጸባረቅበት የድጋፍ ሰልፍ ነው።»

አበበ ቀስቶ በሚል የቅጽል ስም የሚታወቁ አቶ ክንፈ ሚካኤል፣ አቶ አቶ ጉደታ ገለልቻ እና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የድረ ገጽ ጸሀፊ አቶ ስዩም ተሾመን የመሳሰሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ማብራሪያ ያቀረቡት አቀንቃኞች በቅዳሜው ሰላማዊ ሰልፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የማበረታታ ዓላማም የያዘ ነው። የድጋፉ ሰልፍ የየትኛውም ፓርቲ አጀንዳም ሆነ የዘር፣ የሀይማኖት አስተሳሰብ እንደማንጸባረቅበትም የኮሚቴው አባላት ግልጽ አድርገዋል።

Äthiopien Abiy Ahmed OPDO
ምስል Abdulbasit Abdulsemed

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ