1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሦስቱ 2026 ዓ.ም የዓለም ኳስ አስተናጋጆች ታወቁ

ረቡዕ፣ ሰኔ 6 2010

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የጎርጎረሳዉያኑ 2026 ዓ.ም የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታን በጋራ እንደሚያስተናግዱ ታወቀ ። የFIFA ምክር ቤት ዛሬ በሰጠዉ ድምፅ ሦስቱ ሀገራት ሞሮኮን 134/ለ65 በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል።

https://p.dw.com/p/2zVSN
Russland, Moskau: Wahl zum FIFA World Cup 2026
ምስል picture-alliance/AP Photo/A. Zemlianichenko

የ 2026 ዓ.ም የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አስተናጋጆች

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የጎርጎረሳዉያኑ 2026 ዓ.ም የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታን በጋራ እንደሚያስተናግዱ ታወቀ ። ሰሦስቱ ሐገራት የተመረጡት ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ኮንፌደሬሽን FIFA ምክር ቤት ዛሬ በሰጠዉ ድምፅ ነዉ ። የፊፋ ፕሬዚዳንት ጊያኒ ኢንፋንቲኖ የሦስቱን ሃገራት አዘጋጅነት እንዲህ ነበር የገለፁት። 
« የ2026 የፊፋ የዓለም እግርኳስ ዋንጫ አዘጋጅ አሸናፊዎችን አዉቀናል። የማኅበሩ አባላት የሆኑት  ካናዳ ሜክሲኮ እና ዩናይትስ ስቴትስ የ2026 የዓለም እግርኳስ እንዲያዘጋጁ ተመርጠዋል። አመሰግናለሁ» 
የFIFA ምክር ቤት ዛሬ በሰጠዉ ድምፅ ሦስቱ ሀገራት ሞሮኮን 134/ለ65 በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል። ሦስት ሃገራት ለመጀመርያ ጊዜ በጋራ በሚያዘጋጁት የዓለም የእግርኳስ ግጥምያ የ48 ሐገራት ቡድኖች ይካፈላሉ።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ