1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢራን ማዕቀብ ላይ የአዉሮጳ ኅብረት አቋም 

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 2011

በአሜሪካ እና በኢራን በካከል የተጀመረዉ አተካራ ተካሮ እንደቀጠለ ነዉ። አሜሪካንን ጨምሮ ኃያላኑ የአውሮጳ ሃገራት በጋራ ከኢራን ጋር የተስማሙበትን የኒኩሊየር ውል አጥብቀው በመተቸት ሀገራቸውን ከስምምነቱ ያስወጡት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትንትናው ዕለት በኢራን ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። ይህ የትራምፕ ውሳኔ በአውሮፓ ላይ ምን አንደምታ አለው?

https://p.dw.com/p/37ln2
USA P5+1 Gespräche in New York über den Atom-Abkommen mit dem Iran | Mogherini und Zarif
ምስል picture_alliance/dpa/A. Shcherbak

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የጣለችዉ ማዕቀብና የአዉሮጳ ኅብረት አቋም 

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን እና ከኢራን ጋር በሚነግዱ ሐገራት እና ኩባንዮች ላይ ትናንት የጣለችዉን ተጨማሪ ማዕቀብ ቱርክ እንደማታከብር ፕሬዝደንት ጠይብ ኤርዶኻን አስታዉቀዋል። ኢራን በበኩልዋ ከዩናይትድ ስቴትስ አዲስ የተጣለባትን ማዕቀብ እንደማትቀበል አስታዉቃለች። የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ እንደተናገሩት ኢራን የተጣለባትን ማዕቀብ በመሻር ያላትን ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት በቀጣይ ለገበያ ታቀርባለች። «የኤኮኖሚ ጦርነት ላይ ነን» ብለዋል።

ባለፈዉ ግንቦት ወር ከኢራን ጋር የኒኩሊየር ጦር መሳርያ ያለመስራት ዉል የተደረሰዉን ሥምምነት ትራምፕ እምቢኝ ብለዉ በመምጣታቸዉ ከአዉሮጳ ኅብረት ጋር የተለያየ አቋም እንዲይዙ አድርጎአቸዋል። አዉሮጳ እና አሜሪካ በበርካታ ዓለም አቀፍ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በሚወስዱት የተራራቀ አቋም ምክንያት ግንኙነቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወትሮ የነበረውን መልክ እየቀየረ መምጣቱ እየታየ ነው። ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት አንስቶ አውሮጳ እና አሜሪካ በጋራ የገነቡ ያቋቋሟቸውን ተቋማት ሳይቀር ሲያጣጥሉ እና ሲያንኳስሱ የሚታዩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

ትራምፕ አሜሪካንን ጨምሮ ኃያላኑ የአውሮጳ ሃገራት በጋራ ከኢራን ጋር የተስማሙበትን የኒኩሊየር ውል አጥብቀው በመተቸት ሀገራቸውን ከስምምነቱ አስወጥተዋል። በትላንትናው ዕለት ደግሞ በኢራን ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። ከዓመታት ዲፕሎማስያዊ ጥረት በኋላ ከኢራን ጋር የተደረሰበትን ውል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ማጣጣላቸዉ የአዉሮጳ ኅብረት እንዴት ይመለከተዋል? የአውሮጳ ኅብረት ከኢራን ጎን በመቆም የኒኩሊየር ስምምነቱ እንዳይፈርስ የሚያደርገው ጥረትስ ምን ይመስላል? በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ በአውሮጳ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖስ? የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ አለው። ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።   

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ተስፋለም ወልደየስ