1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታንያ የአውሮጳ ህብረትን የምትለቅበት ስምምነት ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011

የአውሮጳ ህብረት በአለማችን ካሉት ጠንካራ የሀገራት ስብስብ መካካል አንዱ ነው። የዚሁ ህብረት አባል የሆነችው ብሪታንያ ከ 60 ቀናቶች በኋላ መጋቢት 20፣ 2011 ዓም በኋላ ህብረቱን ለቃ እንደምትወጣ ይጠበቃል።  የብሪታንያ እና የአውሮጳ ህብረት ፍች በሃገሪቱ ላይ በቀላሉ የማይገመት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል። 

https://p.dw.com/p/3BBYr
Symbolbild EU-Brexit-Gipfel
ምስል picture alliance/dpa

ብሪታንያ የአውሮጳ ህብረትን የምትለቅበት ስምምነት ጉዳይ

ላለፍት ሁለት ዓመታት በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ እንደተሰማው፣ የብሪታንያ እና የአውሮጳ ህብረት ፍች በቀጥታ አልያም በተዘ ዋዋሪ ከሚፈጥረው የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው ጊዚያዊ ጫና የሚያመልጥ ሀገር አይኖርም።ባንድ ወቅት ታላቅዋ ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት ትወጣለች የሚለው ሀሳብ እውን ይሆናል ማለት የማይታሰብ ነበር፣ ነገር ግን የፓለቲካ ድል ለማግኝት ሲሉ ምርጫውን የፈቀዱት የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዲቪድ ካምረን ከሁለት አመት በፊት ህዝባቸው ድምፅ ችንዲሰጥበት የወሰኑት  ከህብረቱ እንውጣ አንውጣ የሚለው ውሳኔአቸው  ሀገራቸውን ከአውሮጳ ህብረት፣ እሳቸውን ከስልጣንቸው ካስወጣ በኋላ ጉዳዩ እስካሁን መነጋገሪያ ፣መነታርኪያ፣ ጣት መጠቆዋቆሚያ እና ማስፍራሪያ ሆኗል። ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር ለ45 ዓመት አብራ ከኖረች በኋላ አሁን ከህብረቱቱ ለመለያየት ያቀረበችው የፍቺ ሰነድ እሰከዛሬ አብረዋት የቆዩት 27 ቱ አባል አገሮች በሙሉ የሚስማሙበት  መሆን አለበት፣ ከዚህ በተጨማሪም ሰነዱ የብሪታንያን ፓርላም ተቀባይነት ማግኘት አለብት ።

Großbritannien Autoproduktion in Solihull
ምስል Getty Images/L. Neal

በብሪታንያ ትላንት 200 በላይ የሚሆኑ ብሬግዚትን የሚደግፍ እና የማይደግፉ የፓርላማ አባላት ጭምር ለጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ ብሪታንያ ያለ ስምምነት የአውሮጳ ህብረትን እንዳትለቅ ደብዳቤ ልከዋል። 585 ገፅ የያዘው የፍቺ ሰነደ በአውሮጳ ህብረት ዘንድ የመጨረሻው የስምምነት ዶስየ እንደሆነ ተነግሮዋል ።
ሜይ ያቀረቡት ይህ ባለብዙ ገፅ ሰነድ ከአንድ ሳምንት በኋላ በብሪታንያ በፓርላማ ድማፅ ይሰጥበታል። የፓርላማውን ተቀባይነት ካገኛ ከ60  ቀናት በሁዋላ መጋቢት 20 ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት በይፋ የምትወጣበት ሰነድ ይሆናል ማለት ነው ።

ጥናት እና ምርምራቸውን ላለፉት 11 አመታት በምህንድስና ላይ ያደረጉት ዶክተድ በላቸው ጨከነ ተስፋ በብሪታንያ የጃግዋር ላንድሮቨር መኪና ማምረቻ መሪ መሀንዲስ፥ የብሪታንያ እና የአውሮጳ ህብረት ፍች ስለሚያስከትለው ችግር ከ«DW» ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተል።
  
ሀና ደምሴ
አርያም ተክሌ