1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውን መብት ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ማቀዱን አስታወቀ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2011

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቀለው የሚገኙ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ማቀዱን ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት የተሰኘው በጎ አድራጊ ድርጅት መስራቾች እና አመራሮች ገለፁ። አመራሮቹ ይህን የገለፁት ዛሬ በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በመገኘት የተፈናቀሉ ዜጎችን በጎበኙበት ወቅት ነው። 

https://p.dw.com/p/3Iqk3
Äthiopien Aktivist Tamagn Beyene
ምስል DW/S. Wegayehu

የግብረ-ሰናይ ድርጅቱ አመራሮች የጌዲዖ ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል

በጉብኝቱ ላይ አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውን መብት ዳይሬክተር እና የመብት ተሟጋች ታማኝ በየነ የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙበት ሁኔታ ስሜትን የሚነካ ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቀለው የሚገኙ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በድርጅቱ በኩል የተጀመረው የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። 
ለጌድኦ ተፈናቃዮች የድጋፍ እጃቸውን ከዘረጉት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ድርጅቱ በቅርቡ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቀለው የሚገኙ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ከ1.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ መለገሱ ይታወቃል። በጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ ማጎ ድርጅቱ በዞኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ላበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 
በዛሬው ጉብኝት ከአለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጲዊያን መብት መስራቾችና አመራሮች በተጨማሪ ወርልድ ቪዥን የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤድዋርድ ብራውንም መገኘታቸውን በስፍራው ተገኝተዋል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ተስፋለም ወልደየስ