1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐረሪ መስተዳድር ሹም ሽር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2011

የቀድሞዉ ርዕሠ መስተዳድር ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት ከአራት ወር  በፊት ነበር።አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር በክልሉ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ነበር

https://p.dw.com/p/37ugb
Gasse in Harer, Äthiopien, mit Moschee im Hintergrund
ምስል picture alliance/dpa

Harrari region-New chief Administrator - MP3-Stereo

የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ እስከ ዛሬ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር የነበሩትን አቶ ሙራድ አብዱላሒን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ ኦሪዲን በድሪን በርዕሠ-መስተዳድርነት ሾሟል።የቀድሞዉ ርዕሠ መስተዳድር ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት ከአራት ወር  በፊት ነበር።አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር በክልሉ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ነበር። ጉዳዩን የተከታተለዉ የድሬዳዋዉ ጋዜጠኛ መሳይ ተክሉ እንደሚለዉ የአዲሱ ርዕሠ መስተዳድር መሾም የተወሳሰበዉን የሐረሪ መስተዳድር ችግር ለማቃለል ይረዳል የሚል ተስፋ አሳድሯል።

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋዓለም ወልደየስ