1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስጳኝ እና የካታላን ውዝግብ

ረቡዕ፣ መስከረም 24 2010

በስጳኝ የካታላን ግዛት ከሀገሪቱ ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ለማወጅ የሚያስችለውን መንገድ ለማመቻቸት ባለፈው እሁድ አከራካሪ ሕዝበ ውሳኔ ካካሄደ ወዲህ በግዛቱ እና በፌዴራዊው መንግሥት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተባብሷል።

https://p.dw.com/p/2lDhi
König Felipe hält Rede an die Nation
ምስል picture-alliance/Casa Real/Europa Press

ንጉሥ ፊሊፔ ሳድሳይ

በሕገ መንግሥቱን የሚጥስ ነው በሚል እንዳይደረግ የተከለከለውን ሕዝበ ውሳኔ ሂደትን እንዲያከላክሉ ማዕከላዩ መንግሥት ወደ ካታላንያ በላካቸው ፖሊሶች እና በግዛቱ ህዝብ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል። ይህን የፖሊስ ርምጃ በመቃወም ትናንት በካታላን ብዙ ህዝብ አደባባይ ወጥቶዋል። እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎም የሀገሪቱ ንጉሥ ፊሊፔ ሳድሳይ ትናንት ለሀገሪቱ ህዝብ ንግግር አድርገዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ