1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀጠለዉ ዉጥረትና ተቃዉሞ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ከአንዱ ወደሌላዉ እየተዛመተ መሆኑን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአዲስ አበባ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1JfUs
Äthiopien Regierung Soldaten ARCHIV
ምስል picture alliance/AP Photo/ltomlinson

[No title]

ዘገባዉ የተቃዉሞ እንቅሴዉን ለማመቅ በመንግሥት ኃይሎች የሚወሰደዉ የኃይል ርምጃ አምባገነኑ የመንግሥት አስተዳደር ያለመርካት ያመጣዉን ተቃዉሞ ወደባሰ አለመረጋጋት ሊመራዉ እንደሚችል ተንታኞች እያስጠነቀቁ ነዉ።

ዛሬም የኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች በርካታ የፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ተሰማርተዉበት ዉጥረት መንገሱ ሲነገር የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣን ደግሞ ከሌላዉ ቀን ዛሬ የሰከነ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል። የአንዱ የሻሸመኔ እንደገለጹልን ወጣቶች ሁለትም ሆነ ከዚያ በላይ ሆነዉ ጎዳና ላይ ከታዩ ለእስር ይዳረጋሉ። አዣንስ ፍራንስ ፕረስ በዘገባዉ የጠቀሳቸዉ የአፍሪቃ ቀንድ ገለልተኛ ተመራማሪ ሬነ ላፎርት፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች የተነሳዉ ተቃዉሞ ምንም እንኳን የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ኃይል እየተጠቀሙ ሊያበርዱት ቢሞክሩም፤ በፈላጭ ቆራጩ የመንግሥት አስተዳደር ያልረካዉን ሕዝብ ብሶት አባብሶ የከፋ አለመረጋጋት ሊያስከትል እንደሚችል ነዉ የጠቆሙት።

Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Deutsch

ሌላዉ የበዴሳ ነዋሪ የነበረዉ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ወጣቶች በብዛት እየታሠሩ በመሆኑ የበረደ ቢመስልም ግን ዉጥረት አለ ይላሉ።አክለዉም ካድሬዎች በየገጠሩ መንደር ሕዝቡ እያሰባሰቡ ማነጋገር መቀጠላቸዉንም ገልጸዋል። በጎንደር እና በባህር ዳር የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች እየታሠሩ መሆኑን አንዳንዶችም ብር ሸለቆ ወደሚባለዉ ስፍራ መወሰዳቸዉን የሚመለከቱ ጥቆማዎችን ይዘን ያነጋገርናቸዉ የአማራ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፀጥታ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ በበኩላቸዉ የዛሬዉን ዉሎ እንዲህ ገልጸዉልናል።

እንደ አቶ በረከት ስምዖን ያሉ የብሔራዊ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ክልሉ በመጓዝ ኅብረተሰቡን እያነጋገሩ እንደሚገኙ እየተነገረ ነዉ። ምናልባት አካባቢዉን ያረጋጋዉ እነሱ በተገኙበት የተደረገዉ ዉይይት ዉጤት ይሆን? ይህ በእንዲህ እንዳለም የአማላ ክልላዊ ርዕሰ መስተዳድር እና የብአዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ ስልጣናቸዉ መገደቡን የሚጠቁሙ መረጃዎችን ጠቅሰን የጠየቅናቸዉ አቶ መኳንንት አንድ መሪ ከኃላፊነቱ ሲነሳ የወከለዉ አካል ተወያይቶ አምኖበት እንደሚሆንም ነዉ የገለጹት። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ.

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ