1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሶሳ ሠላም እና ፀጥታ

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2011

የበኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (በጉሕዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጀመረዉ ስብሰባ እንደቀጠለ ነዉ።ፓርቲዉ እዚያዉ በኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር እና ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ ለተቀጣጠለዉ ግጭት ተጠያቂ በተባሉ ባለሥልጣናቱ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታዉቆ ነበር።

https://p.dw.com/p/39azi
Karte Äthiopien AM

MMT (Q&A) Assossa security - MP3-Stereo

 

ሰሞኑን ሁከት እና ዉጥረት ተጫጭኗት የነበረችዉ የበኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ አሶሳ ከትናንት ጀምሮ አንፃራዊ ሠላም ሠፍኖባታል።ከሁለት ሳምንት በፊት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አገልግሎት ያቆመዉ የአሶሳ ዩኒቨርስቲም ከፊታችን ሠኞ ጀምሮ ማስተማሩን እንደሚቀጥል የዩኒቨርሲቲዉ መምሕራን አስታዉቀዋል።የበኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (በጉሕዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጀመረዉ ስብሰባ እንደቀጠለ ነዉ።ፓርቲዉ እዚያዉ በኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር እና ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ ለተቀጣጠለዉ ግጭት ተጠያቂ በተባሉ ባለሥልጣናቱ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታዉቆ ነበር።ይሁንና ፓርቲዉ ስብሰባዉ ሳይጨርስ የፌደራል ፖሊስ ትናንት አምስት የአካባቢዉን ባለሥልጣናት አስሯል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ