1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ጉዳይ ጉባኤ በአዲስ አበባ

ረቡዕ፣ ግንቦት 8 2010

በአባይ ተፋሰስ ጉዳይ ወደስምምነት ያደርሳል የተባለው የቀጣይ የሦስቱ ሃገራት ባለስልጣናት ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችዉ የሕዳሴዉ ግድብ ግንባታ፤ ግብፅ የውኃው ፍሰት ይቀንስብኛል የሚል ስጋቷን ማሰማቷ በተደጋጋሚ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/2xlRe
Äthiopien Treffen der Aussenminister von Sudan, Ägypten und Äthipien in Addis Abeba
ምስል DW/Getachew Tedla Hailegiorgis

የሦስትዮሹ ጉባኤ በዝግ የሚካሄድ ነው

 ግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያን ያካተተው የሦስትዮሽ ጉባኤ በዝግ የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻው ሥርዓት ብቻ ለጋዜጠኞች ክፍት እንደነበር ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከው ዘገባ ያስረዳል። ዘጋቢያችን በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ የአባይን ውኃ የሚያሳሳት የግብፅ አቋም አሁንም በጥያቄ የሚታይ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ