1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የኦሮሚያ የኤኮኖሚ አብዮት የት ደረሰ?

ረቡዕ፣ ኅዳር 27 2010

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለፈው ዓመት ከፍተኛ የምጣኔ-ሐብት እድገት ያመጣል ያለውን እቅድ ማስተዋወቁ አይዘነጋም።ዕቅዱ ከምጣኔ ሐብታዊ ፋይዳዉ በተጨማሪ በአካባቢዉ የተነሳዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለማቀዝቀዝ፤ ለሕዝቡ በተለይም ለወጣቱ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚረዳ በሰፊዉ ሲነገር ነበር።

https://p.dw.com/p/2ot7r
Äthiopien, Adama
ምስል DW/M. Yonas Bula

የኦሮሚያ የኤኮኖሚ አብዮት የት ደረሰ?

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ላቋቋማቸው የኬኛ መጠጥ ማቀነባበሪያ እና የኦዳ ትራንስፖት ኩባንያዎች ባለድርሻዎችን ማስፈረም ጀምሯል። ኩባንያዎቹ በክልሉ ምጣኔ ሐብት ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የታቀደው "የኤኮኖሚ አብዮት" አካል ናቸው። የተዘጋጁት የመመሥረቻ ድርሻዎች (አክሲዎኖች) በታቀደው መጠን መሸጣቸው ግን አጠራጣሪ ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ሥራ ይገባል የተባለለት ኦዳ የተቀናጀ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ወደ 400 ሺህ በሚጠጉ አርሶ አደሮች እና ባለሀብቶች ባለድርሻዎች ይቋቋማል ተብሎ ነበር።  የኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታከለ ኡማ ባለፈው ቅዳሜ ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ እንደተናገሩት የመመሥረቻ አክሲዮን የገዙት ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ብቻ ናቸው። 

«ለምሳሌ የኦዳን አክስዮን እያስፈረምን እንገኛለን። እስካሁን የባለቤትነት ድርሻ የገዙት ከ10 ሺህ በላይ ናቸው። ዛሬ እስከ 11:30 ወደ 90 በመቶ መስራቾች ፈርመዋል።  ይህን ስንል ወደ አንድ ሺህ ሰዎች ቀርተዋል ማለት ነዉ። በአክሲዮን ድርጅት መመስረቻ ሕጉ መሰረት ድርሻ ከገዙት ዉስጥ አንድ ሰዉ እንኳን ቢቀር ወደ ምሥረታ መሸጋገር አይቻልም። በሌሎች አክስዮኖችም ተመሳሳይ ነገር እያጋጠመን ነዉ። ለምሳሌ የኬኛ ተጀምሯል። ብዙ ሰዎች የኬኛን ድርሻ ገዝተዋል። ይሁን እንጂ ሰዎች ቶሎ ብለው ባለመፈረማቸው  መንጠባጠብ  እያጋጠመን ነዉ።»

የኩባንያዎቹን ምሥረታ በቅርበት ከሚከታተሉት መካከል ዶ/ር ደረጄ ገረፋ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ደረጄ እንደሚሉት ከኬኛ የመጠጥ ማቀነባሪያ እና የኦዳ የተቀናጀ ትራንስፖርት አክሲዮኖች በተጨማሪ የአኳ አምቦ እና የወላቡ የግንባታ ኩባንያ ምሥረታ መንገድ ላይ ናቸው።

ሙሉ ዘገባውን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ