1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዴሞክራቲክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት

ሐሙስ፣ ጥር 2 2011

በጉጉትና ስጋት የተጠበቀው ዴሞክራቲክ ኮንጎ የምርጫ ውጤትታዋቂ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተፎካካሪ እንዳሸነፉበት ይፋ ሆኗል። በተደጋጋሚ ሲራዘም እና ሲጓተት የቆየው የኮንጎ ምርጫ ወትሮም በትርምስ እና ግጭት ውስጥ ለቆየችው ሀገር ሌላ ጣጣ ይዞባት እንዳይመጣ ከሀገሪቱ ዜጎች አልፎ ብዙዎችን ሲያስብ ነበር የሰነበተው።

https://p.dw.com/p/3BKHf
DR Kongo Politiker Felix Tshisekedi
ምስል Getty Images/AFP/T. Charlier

ዛሬ ይፋ የሆነው የምርጫ ውጤት እንደተፈራው ስልጣን ላይ የሚገኘው ፓርቲ እጩን ሳይሆን የተቃዋሚውን ተፎካካሪ ፌሊክስ ቺሴኬዲ ባለድል መሆናቸውን ቢያውጅም የተፈራው ግጭት ግን የቀረ አይመስልም። ሌላኛው የተቃዋሚ እጩ መፈንቅለ መንግሥት ተደርጎብኛል ማለታቸው ደጋፊዎቻቸውን አደባባይ አውጥቶ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አጋጭቷል፤ ከፖሊስም ከማርቲን ፋዩሉ ደጋፊዎች ወገንም የተጎዱ መኖራቸው ተነግሯል። የአፍሪቃ ኅብረት ኮንጎ በውጤቱ ተሰበብ የተፈጠረውን ውዝግብ በአግባቡ እንድትፈታ ጠይቋል። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ