1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጌድኦ ተፈናቃዮች

ረቡዕ፣ ሰኔ 6 2010

እነዚሁ በደቡብ ብሔር ስሄረሰቦች ክልል በጌድኦ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተጠጉ ተፈናቃዮች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ግጭቱ በባህላዊ እርቅ ተፈቶ ነበር። ይሁን እና ዳግም አገርሽቶ ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋል ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

https://p.dw.com/p/2zVUN
Äthiopien Wald
ምስል Imago/blickwinkel

የጌድኦ ተፈናቃዮች ሮሮ

በመጋቢት ወር በጀመረው እና ሰሞኑን እንደገና ባገረሸው በጌድኦ እና በጉጂ ጎሳዎች ግጭት ምክንያት ከኦሮምያ ክልል ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የጌድኦ ብሔረሰብ ተወላጆች በምግብ እጥረት እየተሰቃየን ነው ሲሉ አማረሩ። እነዚሁ በደቡብ ብሔር ስሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በጌድኦ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተጠጉ ተፈናቃዮች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ግጭቱ በባህላዊ እርቅ ተፈቶ ነበር። ይሁን እና ዳግም አገርሽቶ ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋል ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ተፈናቃዮቹ  አሁን በተጠጉባቸው ወረዳዎች በቂ ምግብ እንደማያገኙ ተናግረዋል። ስለ ስሞታው ዶቼቬለ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር ኮሚሽንን አነጋግሯል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ