1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

'ዲጂታል ወያነ' ወይም 'ዲጂታል ትግል'

ሰኞ፣ ጥር 27 2011

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በይፊዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በኩል ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3ChuH
Äthiopien Debretsion Gebremichael, Chairman Tigray People's Liberation Front
ምስል DW/M. Haileselassie

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ የሚደረግ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴም 'ዲጂታል ወያነ' ወይም 'ዲጂታል ትግል' ሲሉ ገልፀውታል፡፡ ምሁራን በበኩላቸው የትግራይ ክልል ገዢ ድርጅትና መንግስት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በኩል ይደረግ የነበረ እንቅስቃሴ በጥርጣሬ ይመለከት እንደነበር በመግለፅ፣ አሁን ፊቱ ወደ ቴክኖሎጂው ማዞሩ የራሱ ገፊ ምክንያቶች አሉት ይላሉ፡፡
የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ባሳለፍነው ቅዳሜ በይፊዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰራጩት የቪድዮ መልእክት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ተሳትፎ የሚያደርጉ ተከታዮቻቸው እያደረጉት ያሉ እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ እንቅስቃሴውም "ዲጂታል ወያነ" ሲሉ ሰይመውታል፡፡ "እስካሁን ባለው በማሕበራዊ ሚድያ በኩል ላደረጋችሁት አድናቆት አለን" በማለት ለተከታዮቻቸው መልእክት ያስተላለፊት ዶክተር ደብረፅዮን የተለያዩ የፖለቲካ ሐይሎች በቴክኖሎጂው 'መታገላቸው' መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ የትግራይ ክልል ገዢ ፖርቲ ህወሓት በማሕበራዊ ሚድያ በኩል የሚደረግ እንቅስቃሴ በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ድርጅት መሆኑ የነገሩ የጋዜጠኝነትና ኮምኒኬሽን ምሁር በበኩላቸው በቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች ወደ ዘዴው እየገባ ነው ብለውናል፡፡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮምኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር ማትዮስ ገብረህይወት የትግራይ ክልል ገዢ ፖርቲ ህወሓት በሜይን ስትሪም ሚድያው ያለው ጫና ለመቋቋም ወደ ማሕበራዊ ሚድያው ትኩረት እያደረገ ነው ብለውናል፡፡

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ኂሩት መለሰ