1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ዋንጫውን ወሰደች

ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2006

የጀርመን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከእርጀቲና ቡድን ጋር ባደረገው የዋንጫ ግጥሚያ አርጀንቲናን አንድ ለባዶ በመርታት የዋንጫ ባለቤት ሆነ። እስከ በመደበኛው የጨዋታ ጊዜ ፍፃሜ ሁለቱ ቡድኖች ባዶ ለባዶ ስለነበሩ ጨዋታው መራዘም ግድ ነበረበት። ከዚያም በ113 ኛ ደቂቃ ማርዮ ገትስ ባስቆጠራት ግብ ነበር ጀርመናውያን ድል ሊቀዳጁ የቻሉት።

https://p.dw.com/p/1CcTL
Fußball WM 2014 Brasilien Deutsche Fußballnationalmannschaft Jubel Pokal
ምስል Reuters

ጀርመን ከ24 ዓመት በኋላ ነበር የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ባለቤት የሆነችው። እንደሚታወሰው እአአ በ1954, 1974, 1990 ዋንጫ አግኝተዋል።

የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ እና መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሪዮ የማራካና ስቴድየም በመገኘት ጨዋታውን ተከታትለውታል። በጀርመን እግር ኳስ አፍቃሪዉ የሀገሩን ባንዲራ በየመኪና፤ ብስክሌቱ እያዉለበለበ፤ ወይም እየለበሰ፤ የሚወደዉን ተጨዋች ምሥል እያነገባ በየአዉራ ጎዳናዉ ሲዘዋወር ነበር የዋለዉ። የፌስታ ማወራረጃዉን (ባብዛኛዉ ቢራ) እየቋጠረ ጨዋታውን በትላልቅ ቴሌቪዥኖች በተሰቀሉበት አደባባዮች ተመልክቶታል። ከግጥሚያው በኋላ ሕዝቡ በየአደባባዩ በመውጣት ደስታውን ሲገልጽ አድሮዋል። አርጀንቲናዎችም ለፌስታ-ድግሥ ቢዘጋጁም አልቀናቸውም። የእግር ኳስ ተንታኞች ዋንጫዉ ከቦይነስ አይሪስ ይልቅ ወደ በርሊን እንደሚሔድ በሰፊዉ ገምተው ነበር።

Fußball WM 2014 Deutschland gegen Argentinien Fans Jubel Deutschland
ምስል Matthias Kern/Bongarts/Getty Images