ሀገር አቀፍ ምርጫ በጀርመን-ዉይይት
እሑድ፣ መስከረም 12 2006ማስታወቂያ
ዲሞክራሲ በሰረፀባቸው የዓለማችን ክፍሎች ምርጫ፦ ሥልጣን ሠላማዊ በሆነ መንገድ ሽግግር የሚደረግበት ሂደት ነው። በአንፃሩ ዲሞክራሲ የሠማይ መንገድ ያህል በራቀባቸው ሃገራት ደግሞ ይኸው ምርጫ፤ አብላጫውን ጊዜ የውዝግብ፣ የመጠላለፍና የመጠፋፋት ወጥመድ ሲሆን ይስተዋላል። ዲሞክራሲ አብቦባቸዋል ከሚባሉ የዓለማችን ጥቂት ሃገራት መካከል ጀርመን አንዷ ናት። የዛሬው የውይይት መድረክ ዝግጅታችን «የፌዴራል ጀርመን የምክር ቤት ምርጫ ምንነት፣ አንድምታ እና አስተምኅሮቱ» የሚል አቢይ ርዕስ ይዟል። ለውይይቱ ሶስት እንግዶችን ጋብዘናል። ዶ/ር ለማ ይፍራሸዋ በጀርመን ሀገር ለረጅም ጊዜ የኖሩ እዚሁ ጀርመንም የተማሩ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር፤ ሌላኛው የውይይቱ ተሳታፊ የፌደራል ጀርመን ዋነኛ ፖለቲከኞች ማዕከል በሆነችው በርሊን ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆነው ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ነው። የአውሮጳ ኅብረት መቀመጫ ከሆነችው ከቤልጂየም ብራስልስ የአውሮጳ ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተለው ሌላኛው ወኪላችን ገበያው ንጉሤም በውይይቱ ይሳተፋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ