1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ 

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 21 2013

የአንበጣ መንጋው ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ በምስራቅ ሐራርጌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ባሌ ዞኖች ከተከሰተ በኋላ በሄሊኮፕተር የታገዘ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳሉት አንበጣው ወደ ተጨማሪ ሶስት ዞኖች የመስፋፋት ስጋት አስከትሏል።

https://p.dw.com/p/3nNuT
Ein Äthiopisches Mädchen versucht gegen die Heuschrecken anzukommen
ምስል Reuters/G. Paravicini

አሳሳቢው ሁለተኛው ዙር የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ

የበረሃ አንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ ዳግም በመስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች በምርት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ። የአንበጣ መንጋው ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ በምስራቅ ሐራርጌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ባሌ ዞኖች ከተከሰተ በኋላ በሄሊኮፕተር የታገዘ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳሉት አንበጣው ወደ ተጨማሪ ሶስት ዞኖች የመስፋፋት ስጋት ቢያስከትልም የሶማሊላነድ እና የኬንያ ድንበር አከባቢን ጨምሮ የመንጋውን ወረራ ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ዘገባ አጠናቅሯል።

ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ