1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለት ዛፍ በሁለት ሺህ ብለን?

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2000

አንዲት አገር ያላትን የብዝሃ ህይወት ስብጥር መጠበቅ ካልቻለች ዛሬ የማይመስለንን ችግር ሁሉ ነገ ግዘፍ ነስቶ በአካል ማየታችን ግድ ነዉ።

https://p.dw.com/p/Ehkf
እየተስተዋል!
እየተስተዋል!ምስል AP

የብዝሃ ህይቀት ጥበቃን ለማጠናከር ዓለም ዓቀፍ ጉባኤያት ይካሄዳሉ ስምምነቶችም ይፈረማሉ። ያንን መካፈልና መፈረሙ ብቻዉን በቂ ሊሆን አይችልም፤ ተግባራዊ ርምጃ ሲወሰድ እንጂ።

ዛሬ ዛሬ ተፈጥሮ በሚፈፀምባት አግባብ የሳተ ድርጊት ሳቢያ አመጿን ስታሳይ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ አብረዉ የመሄዳቸዉ ነገር ግድ መሆኑን ማመላከቱ ይመስላል። በአንድ አካባቢ የታሰበ የልማት ተግባር የአካባቢዉን ይዞታ ብሎም በኗሪዎቹ ህይወት ላይ ሊያስከትለዉ የሚችለዉ አሉታዊ ተፅዕኖ ከግምት ሊገባ እንደሚገባዉ ባለሙያዎቹ ደጋግመዉ አንስተዉታል። ያ ግን ሲደረግ አይታይም።