1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለት የኢትዮጵያ የማራቶን ሯጮች መታገድ

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ሐምሌ 13 2008

ባሳለፍነዉ ሳምንት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ሁለት የማራቶን ሯጮች > የተሰኘ ኃይል ሰጪ ንጥረ-ነገር መጠቀማቸዉ በምርመራ ተረጋግጧል በሚል ለአራት ዓመት ከሩጫ መታገዳቸዉን በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1JShO
Doping Symbolbild
ምስል picture-alliance/dpa/P. Seeger

[No title]

እንደ መግለጫዉ ከሆነም፣ ጣኢሞ ሹሚዬ የተባለችዉ አትሌት ባለፈዉ መስከረም በተደረገባት ምርመራ ናድሮስትሮኔ የተሰኘዉን ንጥረ ነገር መዉሰዷ ሲረጋገጥ፣ ሌላኛዉ አትሌት ስንታየዉ መርጋ ደግሞ በታህሳስ ወር ዉስጥ በተደረገዉ ምርመራ 19-ኖራንድሮስቴኔዲኦን የተሰኘዉን ንጥረ ነገር መዉሰዱ ታዉቋል። ለሁለቱም የተሰጠዉ የአራት ዓመት እገዳም ከጥር ወር ጀምሮ እንደፀናም መግለጫዉ ያሳያል።


የኃይል ሰጪ ንጥረ-ነገሮችን ተጠቅመዋል ተብሎ ምርመራ ሲካሄድባቸዉ የነበረ ሰባት አትሌቶች ቢሆኑም ሁለቱ ላይ ብቻ የእግድ ቅጣቱ ብወሰንም ቀርዎቹም በተመሳሳይ ምርመራ ኢየተደረገባቸዉ መሆኑን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ስለሺ ብስራት ለዶጬ ቬሌ ተናግረዋል።

ይህ ርምጃ በአገሪቱ የአትሌትኪስ ድባብ ዉስጥ ተፅዕኖ አሳርፏል አሳርፈዋል ስልም የስፖርት ጋዚጤኛ ምስጋናዉ ታደሰ ተናግራዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን በብራዚል የሚካሄደዉ የሪዮ 2016 ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ ከ35 የማያንሱ አትሌቶችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ለማሳተፍ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቁ የሚናገሩት አቶ ስለሺ ከኃይል ሰጪ ንጥረ ነገሮች ጋር በተገናኘ ፌዴሬሼኑ ቀደም ብሎ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንደሠራ እና ከስነልቡና ጋር በተያየዘም አትሌቶቹ ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸዉም አብራርተዋል። ይሁን እንጂ አሁን የተወሰደዉን ርምጃ አስመልክቶ ጋዜጠኛ ምስጋናዉ አንዳንድ አትሌቶችን አነጋግሮ ግማሽ ምን ይገኝብኛል የምል ፍራቻ ብኖራቸዉም ግማሹ ደግሞ እልህ እንደተያያዙ ይናገራል።

በዚህ ጉዳይ ላይ በደረ ገጻችን ላይ አስተያየታቸዉን ከሰጡን መካከል <<ከባህር ላይ ውኃ እንደ መጨለፍ ያህል ነው>> የሚሉ የመኖራቸዉን ያህል <<እንደውም ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ራሱ መልካም ነው>> ያሉም አልጠፉም። ሌሎች ደግሞ ይህ <<እስካሁን የነበረንን መልካም ስም በመጠኑም ቢሆን ያጎድፈዋል>> ብለዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ