1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለት ጊዜ የተራዘመዉ 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2011

ከአንድም ሁለት ጊዜ የተራዘመውና መች እንደሚከናወን ገና በውል ውሳኔ ያላገኘው 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ምንም እንኳን በጊዜ ገደቡ መከናወን ባይችልም አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲከናወን ይሰራል ሲል ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለዶቼ ቬለ «DW» ተናግሯል፡፡

https://p.dw.com/p/3GdV0
Karte Sodo Ethiopia ENG


ከአንድም ሁለት ጊዜ የተራዘመውና መች እንደሚከናወን ገና በውል ውሳኔ ያላገኘው 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ምንም እንኳን በጊዜ ገደቡ መከናወን ባይችልም አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲከናወን ይሰራል ሲል ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለ« DW » ተናግሯል፡፡ ቆጠራው እንዲራዘም ሲወሰን ሰፊ ክርክር ተደርጎና በወቅቱ ቢከናወን በሃገሪቱ ላይ ለሌላ ቀውስ መጋበዝ መሆኑን ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ፌዴራል መንግስት አምነውበት መወሰኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ተናግረዋል፡፡ ከምንም በላይ ግን በሃገሪቱ የጸጥታ መጓደል በየቦታው ከቀያቸው የተበተኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለመቻሉ ቆጠራውን ለማራዘም ገፊ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ቆጠራው መራዘሙ ሲሰማ የቆጠራ መሳሪያውን ወደየ ቤታቸው ይዘው ሄደው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚደርሱ ሰራተኞችም አሁን ንብረቶችን መልሰው ገቢ አድርገዋል ብለዋል ሃላፊው፡፡


ሰለሞን ሙጬ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ