1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሃኛያዉ ዓመት የጀርመን ዉሕደት-ከስታስቲክሱ ባሻገር

ሰኞ፣ መስከረም 24 2003

የጀርመን ዉህደት ቢሰምርም፣ በጀርመናን መገናኛ ብዙሃን እንስካሁን የጀርመን ዉህደት ስኬትን በተመለከተ የዉደሳ ዘገባ ተሰምቶ አያዉቅም። ከዉህደቱ ስኬት ዉደሳ ይልቅ ዉህደቱ ያስከተለዉን ችግር በማማረር ሲኮንን ብቻ ነዉ የሚሰማዉ፣

https://p.dw.com/p/PPZW


በጀርመን ዉህደት ታሪክ ያለፈዉ ሃያ አመት በርግጥ ብዙም ሳይታወቅ ነዉ ያለፈዉ።ጀርመን ዳግም የተዋሐደችበት ሃያኛ ዓመት ክብረ በአል ሲዘከር፣ የተደረሰበትን ታሪካዊ እድገት ማወደስ ብቻ ሳይሆን ሊተች የሚገባዉም ይመስለኛ ሲል የዶቸ ቬለዉ ባልደረባ ስለ ጀርመን ዉህደት እና እድገትዋ ማርክ ኮህ ሃተታዉን ይጀምራል።

ለጀርመን ዉህደት ሃያኛ አመት ክብረ በአል ጥናታዊ አሃዞች የበላይነትን ይዘዉ ይገኛሉ። የጥናት መረጃዎች እና የቁጥር መዘርዝሮች ጀርመን ከዉተዋሃደችበት ከሃያ አመት በኋላ፣ ዛሬ በእድገትዋ ምን ቦታ ላይ ደርሳለች፣ ለሚለዉ መልስ አላቸዉ። አብዛኞቹ የመረጃ መዘርዝሮች፣ ባለፉት ሃያ አመታት ምን አይነት ስህተቶች እንሰተሰሩ፣ ለምሳሌ በተዋሃዱት በአዲሶቹ የጀርመን ክፍሎች ዉስጥ ፍትህ የጎደለዉ ነገር እንደሚታይ፣ በምስራቁ የጀርመን ክፍል ያለዉ የስራ አጥ ቁጥር ምዕራብ ካለዉ በሁለት እጥፍ እንደሚጨምር፣ እንዲሁም በምዕራባዊ ጀርመን ያለዉ ህዝብ፣ በምስራቅ የሚኖረዉ ህዝብ ለሚሰራዉ ተመሳሳይ ስራ እጥፍ ደሞዝ እንደሚያገኝ የመሳሰሉትን መረጃዎች ያትታሉ። ሌሎች ጥናታዊ ጽሁፎችንም ማንበብ ይቻላል። ግን ይህ ሁሉ መዘርዝር ስለ ጀርመን እና ስለ ዉህደትዋ በርግጥ በትክክል ይገልጻል? ብዙም አይመስልም።


ልዩዉ ታሪክ

ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ጀርመንን ዳግም ለመገንባት የተጀመረዉ እና አሁንም ተፈጻሚነት ያላገኘዉ ስለ ትልቁ መዋቀር ስኬት እና ሂደት በቁጥር መዘርዝር ማስቀመጥ አይቻልም። በቀድምዋ ምዕራብ ጀርመን ያለዉ ህዝብ ምስራቅ ጀርመንን ለመገንባት እስካሁን የከፈለዉን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ግንባታዉ እስኪጠናቀቅ መክፈሉን ገና ይቀጥላል። ታድያ በእርግጥም ይህ በኢኮነሚዉ ላይ ችግርን ሳያመጣበት አልቀረም። በምስራቅ ጀርመን የሚኖረዉ ህዝብም፣ የለመደዉን አይነት የኑሮ ዘዴ እርግፍ አድርጎ በአንድ ጊዜ እንደ ምዕራቡ ህዝብ እንዲኖር መታሰቡ፣ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሐብቱም ተስተካክሎ እንዲኖር መደረጉ የበለጠዉን ዉጥረት እና ችግርን ሳያሳድርበትም አልቀረም።ይህ ሁሉ ሆኖ የጀርመን ዉህደት ቢሰምርም፣ በጀርመናን መገናኛ ብዙሃን እንስካሁን የጀርመን ዉህደት ስኬትን በተመለከተ የዉደሳ ዘገባ ተሰምቶ አያዉቅም። ከዉህደቱ ስኬት ዉደሳ ይልቅ ዉህደቱ ያስከተለዉን ችግር በማማረር ሲኮንን ብቻ ነዉ የሚሰማዉ፣ ምንም እንኳ ትችቱ ትክክለኛ ሳይሆን የተጋነነ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ቢሆንም። የተለያየ የፖለቲካ ርዮተ አለም የነበራቸዉ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመን፣ ከሃያ አመት ዉህደት በኋላ ይህን ያህል በአንድ ያብባሉ ያድጋሉ ብሎ የገመተ አልነበረም። በሌላ በኩል ከሃያ አመት በኋላ፣ ዛሬ በሁለቱ የጀርመን ግዛቶች መካከል ምንም አይነት ልዩነት መታየት የለበትም የሚል ካለ-እሱ የዚህን ታላቅ የታሪክ ክስተት ገና አልተገነዘበም ወይም አልተረዳም ማለት ነዉ።

Deutsche Welle Chefredakteur Marc Koch neu
ማርክ ኮሕ-የዶቸ ቬለ ዋና አዘጋጅምስል DW


ለሙከራ በቂ ጊዜ አልነበረም

ጀርመንን ምስራቅ እና ምዕራብ ለሁለት የከፈለዉ ግንብ ከፈረሰ እና ከዉህደቱ እስከ ጥቅምት ሶስት (እጎአ) ባለዉ ጊዜ ብዙ ስህተት መሰራቱ ወይም ነገሮች በትክክል አለመገመታቸዉ የማይካድ ቢሆንም በዚያን ጊዜ ሁለቱን የጀርመን ግዛቶች ለማዋሐድ መረሃ-ግብር አዉጭዎቹ ጊዜዉን ጠብቀዉ ዉሕደቱን በተገቢዉ መንገድ ለማከናወን በቂ ጊዜ አልነበራቸዉም።ከዚሕ ይልቅ በጊዜዉ ያጋጠማቸዉን ታሪካዊ ክስተት ተጠቅመዉ ተቃራኒ ርእዮተ-አለም የሚከተሉ ሁለት ሐገራትን ለማዋሃድ መጣደፍ ነበረባቸዉ፣ ተሳክቶላቸዋል። ጥሩም ሰርተዋልም።የያኔዉ የጀርመን መራሔ-መንግሥት ሔልሙት ኮል እ.ጎ.አ በ1990 ሁለቱ ጀርመኖች ከተዋሃዱ ከጥቂት አመት በኋላ፣ በግዛቶች መካከል ያለዉ ልዩነት ፈጽሞ የማይታይ ወጭዉም የማከብድ እና የማይጎዳ ይሆናል ብለዉ ተቻኩለዉ ለህዝብ ቃል መግባታቸዉ በርግጥም የተጋነነ ነበር። ለጀርመን ዉህደት የተጉት ኮልና የካቢኔ አባሎቻቸዉ፣ ይህ የገቡት የማይሆን ቃላቸዉ፣ አሁን ሊፍቁት የማይችሉት፣ ቀላል እና ክብደት የማይሰጠዉ፣ የመወያያ ርእስ ሆኗል።


ያም ሆኖ ግን በሁሉም መስክ ሲታይ ጀርመን በመዋሃድዋ በጣም ተጠቃሚ ሆናለች! ጀርመን ከሃያ አመት ዉህደት በኋላ ሁለገብ እና ግልጽ የሆነች ህዝቦችዋ በደስታ የሚኖሩባት፣ በተቃራኒ ነገሮች ላይ ክርክር በማድረግ እና ግልጽ የሆነ መፍትሄ በማግኘት፣ ለማህበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሄ በማግኘት የምትራመድ አገር ሆናለች። መፍትሄ የምታገኘዉ ተሸፋፍና ሳይሆን፣ ግልጽ በሆነ መንገድ አስባና አይኖችዋን ከፍታ በመጠየቅ ሆኗል። በዚህም ጀርመን በማሃል አዉሮዻ የምትገኝ በማያቋርጥ ለዉጥ ላይ ያለች፣ ከብዙ ፈተናዎች፣ ከብዙ ሙከራዎች እና ልምዶች ጋር በመራመድ ላይ ያለች ቤተ ሙከራ ናት። ይህም አንዱ የዉህደቱ ዉጤት ነዉ። ይህ ነዉ ከእስታቲክሱ ይልቅ ስለጀርመን ዉህደት ስኬት በትክክልና በግልጽ የሚያስቀምጠዉ።

ዴኒስ ሽቱተ
አዘብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ