1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሃዉሳ ቋንቋ

Azeb Tadesseሰኞ፣ ነሐሴ 28 1999

አፍሪቃ በምዕራባዉያን ቅኝ ግዛት በወደቀችበት ዘመን በምዕራባዉያኑ ዘንድ የሚነገሩ ቋንቋዎች እንደ እንጊሊዘኛ ጀርመንኛ ፈረንሳይኛ፣ የስፓኝ ቋንቋ፣ ጣልያንኛ የፖርቱጋል ቋንቋ የኔዘርላን ደች ቋንቋ፣ በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች በስፋት ከመነገራቸዉም በላይ በአፍሪቃ ዉስጥ 2000 ሺህ ያህል አፍሪቃ ወለድ ቋንቋዎች እንዳሉ ጽሁፎች ያስረዳሉ።

https://p.dw.com/p/E0mB
የናይጀርያ ሴት
የናይጀርያ ሴትምስል AP

ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል ኪስዋሂሊ፣ አማርኛ እና የሃዉሳ ቋንቋዋ በአፍሪቃችን በሰፊዉ ይነገራል። የዶቸ ቬለ ራድዮ ጣብያ በሃዉሳ ቋንቋ በየቀኑ ለመካከለኛዉ እና ለምዕራብ አፍሪቃ ስርጭቱን ያሰማል። ሰሞኑን የዶቸ-ቬለ ራድዮ የሃዉሳ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ለአድማጮቹ፣ በሃዉሳ ቋንቋ ዉስጥ ተወዳጅ ቃል የቱ ነዉ ሲል የመዘርዝር ጥያቄ አቅርቦ፣ በርካቶች ይህ በሃዉሳ ቋንቋ ተወዳጅ ነዉ፣ ሲሉ መልሳቸዉን አሰምተዋል። ተወዳጅ ቃል በሃዉሳ ምን ይሆን የስርጭት ክፍሉን ሃላፊ አነጋግረናል። በተጨማሪ ስለ በሃዉሳ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዘንድ ያለ የሰርግ ባህል ልናወራችሁ ተዘጋጅተናል