1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሃያኛዉ ዓመት የጀርን ዉሕደት-ከሃያ አመት በኋላ II

ዓርብ፣ መስከረም 21 2003

በምስራቁ ክፍል ያለዉ የስራ አጥ ቁጥር ከምዕራቡ 11.5 በመቶ ይበልጣል። እ.ጎ. አ በ1990 በዚሁ በፍራንክፈርት ኦደር አካባቢ 88,000 ያህል ህዝብ ይኖር ነበር። ከዉህደቱ በኳላ ግን ህዝቡ በየቦታዉ ተሰዶ የቀረዉ 30,000 ያህል ነዋሪ ብቻ ነዉ

https://p.dw.com/p/PRsK
ፍሎሪያ፤ኬቲ እና ዮርንምስል Benjamin Hammer

በምስራቅ ጀርመን የሚኖረዉ ወጣት ከ 20 አመት ዉህደት በኋላ በምዕራብ ጀርመን ከሚኖረዉ ወጣት የተለየ ኑሮ እንደማይኖር ተገንዝቧአል፣ የሚኖረዉም በአዲሲቷ ጀርመን ዉስጥ ነዉ። ግን በአብዛኛዉ ምስራቅ ጀርመን የሚኖሩ ተማሪዎች ምዕራብ ጀርመን ባለ ትምህርትቤት ዉስጥ መማርን ይፈልጋሉ።

ጀርመን ዉስጥ ፍራንክፈርት የሚባሉ ሁለት ከተሞች አሉ። የመጀመርያዉ አብዛኞቻችን ኢትዮጽያዉያን የምናዉቀዉ በምዕራብ የምትገኘዉ ፍራንክፈርት አም ማይን፣ ትልቁ አለም አቀፉ አዉሮፕላን ጣብያ የሚገኝባትን ሲሆን ሁለተኛዋ ፍራንክፈር ኦደር በጀርመንኛዉ (ፍራንክፉርት አን ዴር ኦደር) የተሰኘችዉን በምስራቅ ጀርመን ፖላንድ ጠረፍ የሚትገኘዉን ከተማ ናት።
ብዙዎቹ ምዕራብ ጀርመን ነዋሪዎች ፋራንክፈርት ኦደር፥ በርካታ ስራ አጥ የሚገኝባት፣ ለኑሮ የማትሆን የተበለሻሸች ሥፍራ ነች ብለዉ ያምናሉ። በካርል ሊብክኔሽት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማረዉ የ17አመቱ ፍሎርያን « ጋዜጠኛ ስለኛ ሲዘግብ በአካባቢዉ የስራ አጥነት እና ቀኝ አክራሪዎች ብቻ እዳሉ ነዉ የሚጽፈዉ በዚህም ስለ ፍራንክፈርት ኦደር ማንም ጥሩ ነገር አያስብም» ሲል ይገልጻል።

Hochwasser in Ostdeutschland Frankfurt an der Oder
ፍራንክፈርት ኦደርምስል picture alliance/dpa

ፍሎርያን ከ18 አመትዋ ካቴን እና ከ16 አመቱ ዮርን ጋር ቆመዉ ያወራሉ። ሶስቱም በዚህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ አመት ተማሪዎች ናቸዉ። ካሉበት አካባቢ ብዙም ሳይርቅ ከምትገኘዉ ከፖላንድዋ የስሉቢሴ ከተማ ከማሪየን ቤተክርስትያን የሚጮኸዉ ደዉል ይሰማል። « በእዉነቱ አካባቢዉ ዉብ ነዉ፣ ከዚሕ የበለጠ ጥሩ ነገር መስራትም ይቻል ነበር» ሲል ይገልጻል ፍሎርያን «ነገር ግን ህዝብ ቦታዉን እየለቀቀ ወደሌላ ቦታ እየፈለሰ ነዉ» አከለ።


30,000 ያህል ህዝብ ፍራንክፈርት ኦደርን ለቆ ሄድዋል።

Schüler des Karl-Liebknecht-Gymnasiums in Frankfurt (Oder)
የካርል-ሊበክኔኽት ት/ቤት ተማሪዎችምስል DW

በፍራንክፈርት ኦደር ያሉ ወጣቶች ስለ ጀርመን ዉህደት ሲያስቡ ስለ ፖለቲካ አልያም ስለ ታሪክ ሳይሆን ወደፊት ስለሚሆኑት፣ ስለሚደርሱበት ነገር ነዉ የሚያዉጠነጥኑት። በምስራቁ ክፍል ያለዉ የስራ አጥ ቁጥር ከምዕራቡ 11.5 በመቶ ይበልጣል። እ.ጎ. አ በ1990 በዚሁ በፍራንክፈርት ኦደር አካባቢ 88,000 ያህል ህዝብ ይኖር ነበር። ከዉህደቱ በኳላ ግን ህዝቡ በየቦታዉ ተሰዶ የቀረዉ 30,000 ያህል ነዋሪ ብቻ ነዉ። ወጣቶቹ ጀርመናዉያን ካትዪ፣ ዮረን እና ፍሎሪያንም እንዲሁ ምዕራብ ሄደዉ መኖርን ይመርጣሉ። ፍሎርያን በዩኒቨርስቲ የባቡር ስራ ትምህርትን ነዉ ማጥናት የሚፈልገዉ። ይህን ትምህርት በምዕራቡ ክፍል ዉስጥ ነዉ መከታተል የሚችለዉ «ይህ ትምህርት ቢኖር ኖሮ እዚሁ ብቀር ነበር የምሻዉ» ይላል እሱ

ከሃያ አመት በኳላ በተለይ በወጣቱ ምናልባትም በወር ገቢ ደምወዝ ይሆናል እንጂ ሌላ ልዩነት አይታይም። ወጣት ዮርግም «የተከፈልን ጀርመናዉያን አይደለንም» ይላል። «አሁንም ስለግንቡ ስለመከፈሉ ይታወሳል፣ ግን ሁሉ ነገር ቀስ እያለ ይቀራል» በጀርመን ዉስጥ በአሁኑ ወቅት ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በእድሜያቸዉ ተከፋፍላ ስለነበረችዉ ጀርመን ሳይሆን አንድ ስለሆነችዉ ጀርመን ብቻ ነዉ የሚያዉቁት። ይኸዉም እነዚህ ተማሪዎች በሙሉ የተወለዱት ከአዉሮጳዉያኑ 1992 እስከ 1994 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ነዉ።


የምዕራብ እና የምስራቅ ጀርመን ወጣቶች መመሳሰል


ታዋቂ የሙዚቃ ባንድ፣ ታዋቂ የስፖርት ቡድን አልያም ተወዳጅ የመዝናኛ ስፍራ የመሳሰሉት ምርጫዎች ላይ የምዕራብ እና የምስራቅ ጀርመን ቡድኖች ምርጫቸዉ አንድ ሆንዋል። የ TNS የምርምር ጣብያ ባልደረባ ቶማስ ጌንስኬም በምስራቅ እና በምዕራብ ጀርመን ባሉ የተለያዩ ትዉልዶች ላይ ጥናት አድርገዉ ወጣቱ ትዉልድ ካለፈዉ ትዉልድ እጅግ በበለጠ ሁኔታ እንደሚመሳሰል ይገልጻሉ። ጀርመናዊዉ ቶማስ ጌንስኬ ከልጅነት እስከ እዉቀት በምስራቃዊዉ ማግድቡርግ ከተማ ከዝያ ከዉህደቱ በኳላ ምዕራቡ ጀርመን መኖር መጀመራቸዉ የጥናታቸዉ ዋና መንደርደርያ ነጥብም አድርገዉታል።
በፖለቲካ አንጻር ለምሳሌ የምስራቁን ወጣት ዲሞክራሲዉ ጥሩ እንደሆነ ኢጠየቅ፣ ገና ሊስተካከል የሚገባዉ ነገር እንዳለ ይገልጻል። በምዕራቡ የጀርመን ክፍል የሚሰራት መዋቅር በምስራቁ ክፍል አዲስ በመሆኑ አሁንም በምዕራቡ እና በምስራቁ ክፍል በማንኛዉንም ጉዳይ ላይ ልዪነት መገኘቱን አይቀሪ ነዉ።

Wohnhäuser in der Innenstadt von Frankfurt (Oder).
የፍራንክፈርት ኦደርን መኖሪያ ቤቶችምስል DW

በዉህደቱ ደስተኞች ነን

ሁለቱ የጀርመን ክፍሎች በመዋሃዳቸዉ ቅር የሚለዉ አለ? ለሚለዉ ጥያቄ የሊብክኔሽት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፍጹም ነዉ መልሳቸዉ። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዋ ኢንካ ሶሪስ« አንድነት እና ዉህደት በመኖሩ በጣም ደስተኞች ነን፣ በምስራቅ ጀርመን ያለን ከዉህደቱ በፊት ከአገር አገር እንደልባችን መዘዋወር አንችልም ነበር» ስትል ትገልጻለች።
ከምራስቅ የመጣ ከምዕራብ የመጣ የሚለዉ አነጋገር ዘዪም የተለመደ ብዙ ግዜ ጥቅም ላይ የሚዉል ቦታን ከመግለጽ ባሻገር ምንም ማለት አለመሆኑም ታዉቆአል።

ቤንያሚን ሐመር

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ